ሰው ሰራሽ አስተውሎት ​ለጤናው ዘርፍ ተስፋ ወይስ ስጋት?

10

 

ባሕር ዳር: መስከረም 14/2019 ዓ.ም (አሚኮ) ሰው-ሰራሽ አስተውሎት በግብርና፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ እና በንግድ ዘርፎች ውስብስብ ችግሮችን እየፈታ ነው። ምርታማነትን በማሳደግ እና የሰውን ልጅ ድካምም በእጅጉ እያቀለለ ነው።

ጎን ለጎን ቴክኖሎጂው በጥንቃቄ የሚታለፋ ስጋቶች መያዙ ሳይረሳ ማለት ነው።

👍ሰው ሰራሽ አስተውሎት በጤናው ዘርፍስ ምን ተስፋ እና ስጋት አመጣ?

​የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የላቁ ሰው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎች በጤናው ዘርፍ ብዙ ጥቅሞች እንደሚሰጡ አስቀምጧል።

-ከእነዚህም ውስጥ፦

#የሕመም ምርመራ እና እንክብካቤ፦
​የህሙማንን የጽሑፍ ጥያቄዎች እና የሕመም ምልክቶች በመተንተን ፈጣን የምርመራ ድጋፍ መስጠት።

#በህሙማን የሚደረግ ፍተሻ፦
ህሙማን የራሳቸውን የሕመም ምልክቶች እና ሊወሰዱ የሚገባቸውን ሕክምናዎች በራሳቸው እንዲረዱ ማገዝ።

#የአሥተዳደር እና የጽሕፈት ሥራዎች፦
​የህሙማንን የሕክምና ታሪክ ማዘጋጀት እና ማጠቃለል፤ የዶክተሮችን እና የነርሶችን የጽሕፈት ሥራ ጫና ማቃለል፤

#የሕክምና እና የነርሲንግ ትምህርት፦
​ለተማሪዎች እና ለጤና ባለሙያዎች በተግባር የተደገፈ የተመስሎ (Simulated) ሥልጠና መስጠት።

ይህ ​በቀላል ምሳሌ ሲገለጽ አንድ የሕክምና ተማሪ አደገኛ የኾነ የቀዶ ሕክምና ከመስራቱ በፊት፣ የኮምፒውተር ፕሮግራም (AI) በሚፈጥርለት “ምናባዊ ታካሚ” ላይ ስህተት ቢሰራ እንኳ ሰው ሳይጎዳ ደጋግሞ እንዲለማመድ የሚሰጥ ተግባራዊ ሥልጠና ነው።

#ሳይንሳዊ ምርምር እና የመድኃኒት እድገት፦ አዳዲስ የመድኃኒት ውህዶችን እና ፈውሶችን ለማግኘት የሚደረጉ ምርምሮችን ማፋጠን።

✍️የሚጠበቁ ሥጋቶች፦

​የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ሰው ሰራሽ አስተውሎት በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ሁሉ ስጋትም አለው ይላል።

​#የተሳሳቱ መረጃዎች፦ ኤአይ (AI) አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ የተሳሳተ ወይም ያልተረጋገጠ የሕክምና መረጃ እንደ እውነት አድርጎ ሊያቀርብ ይችላል።

​#ሰው በተሳሳተ መረጃ ተነሳስቶ የተሳሳተ መድኃኒት ሊወስድ ይችላል።

​#አድሏዊ አሰራር /የመረጃ መዛባት፦ ኤአይ የሰለጠነው በአብዛኛው የነጭ ሕመምተኞችን መረጃ ብቻ በመጠቀም ነው። ይህም የጥቁር ሕሙማንን የሕመም ምልክት በትክክል ላይረዳ ወይም የተሳሳተ ውሳኔ እንዲሰጥ ያደርገዋል።

​#በቴክኖሎጂው ላይ ከመጠን በላይ መተማመን፦ «ኤአይ አይሳሳትም» ብሎ በማመን፣ የኤአይ መሣሪያው የሚናገረውን ሁሉ ያለ ምንም መጠራጠር እና ፍተሻ እውነት አድርጎ መቀበል ነው።
​
​#የሳይበር አደጋ እና የመረጃ ምሥጢር መውጣት፦ የህሙማንን የሕክምና ታሪክ፣ የራጅ ፎቶዎች እና የግል መረጃዎች በኢንተርኔት ላይ ስለሚቀመጡ በሌቦች (ሃከሮች) ሊሰረቁ ይችላሉ።
​
​የዓለም ጤና ድርጅት እንደገለጸው ጀነሬቲቭ ኤአይ የሕክምና አገልግሎትን የማሻሻል ከፍተኛ አቅም አለው፤ ነገር ግን አደጋዎቹን በጥንቃቄ ተረድቶ መምራት እንደሚያስፈልግም አመላክቷል።

መንግሥታት፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና የጤና ባለሙያዎች በጋራ በመኾን የቴክኖሎጂውን አጠቃቀም በኃላፊነት ሊመሩት እንደሚገባ አሳስበዋል።

Previous article“እናቶች ማቅ አውልቀው ሸማ ይልበሱ፤ ሕዝብም እፎይ ይበል”
Next article‎ባሕር ዳር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ እንግዶችን ለመቀበል ተዘጋጅታለች።