“እናቶች ማቅ አውልቀው ሸማ ይልበሱ፤ ሕዝብም እፎይ ይበል”

68

ባለፉት ዓመታት በአማራ ክልል ያጋጠመው ግጭት ዘርፈ ብዙ ጉዳት አስከትሏል። የክልሉን ሕዝብ ለከባድ ማኅበራዊ ቀውስ፣ ለከፋ ስቃይ እና እንግልት ተዳርጎ ቆይቷል። ብዙ ንጹኃንን የሕይወት መሥዋትነት አስከፍሏል፤ የከበረው የሰው ደም በከንቱ ፈስሷል።

📌ለመኾኑ በግጭቱ ማን ተጎዳ? ማንስ አተረፈ?

ግጭቱ በወንድማማች መካከል የተፈጠረ ነው። አስቡት እስኪ የባለፉት ዓመታት የመጠፋፋት ጊዜ ስንቱን እንዳሳጣ?

ግጭቱ በጥቂቶች እና በጦር ግንባር ላሉት ብቻ ሳይኾን በእያንዳንዱ ቤት ገብቶ የበርካቶችን ሕይወት አጨልሟል፣ ኑሮን አመሰቃቅሏል። የሕዝብ መገልገያ መሠረተ ልማት ጎድቷል። ወላድ እናቶች ሕክምና ሳይደርሱ በምጥ አለንጋ ተገርፈውበታል።

በርካታ ሕጻናት ያለ አሳዳጊ ቀርተዋል። እናቶች ማቅ ለብሰው አልቅሰዋል። ያለ ጧሪ ቀባሪ የቀሩ አረጋውያንም በርካቶች ናቸው።

🚸ነገን በስስት የሚጠብቁ ሕጻናት በለጋ እድሜያቸው መቦረቅ ሲገባቸው በጥይት ድምጽ የሥነ ልቦና ጫና ደርሶባቸዋል። ትምህርት ቤት መዋል ሲጠበቅባቸው በጦርነት ቀጣና ታጉረው ኖረዋል።

ይህንን ግጭት ለማስቆም፣ ሰላምን ለመመለስ ሰፊ ጥረቶች ተደርገዋል። በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮች ቀርበዋል። በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የግጭቱን ጉዳት በውል የተረዱት ታጣቂዎችም የሰላም አማራጭን ተቀብለው እየገቡ ነው።

በተለይም በሰሜን ጎንደር እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ከሰሞኑ በርካታ ታጣቂዎች ገብተዋል። በጃናሞራ ወረዳ አካባቢ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት ታጣቂዎች መካከል ሀሳቡን ያካፈለን የቀድሞው ታጣቂ በተሳሳተ መንገድ ጥቅም በሌለው ትግል ውስጥ መቆየታቸውን በመጸጸት ይናገራል።

“አሁን ደስ ብሎን የሰላም አማራጭን ተቀብለናል፤ ሕዝብ እንዳይበደል ዳር ድንበራችን እንዲከበር ለሀገራችን በጋራ ለመቆም መርጠናል። ሌሎች በጫካ ያሉ ኅይሎች እንዲመጡም ጥረት እናደርጋለን” ብሏል 🇪🇹✨

ሌላኛው ሀሳቡን ያጋራን የቀድሞ ታጣቂ እንደተናገረው በተለያየ ምክንያት ለትጥቅ ትግል ወደ ጫካ የገቡበት ትግል እንዳሰቡት አልኾነም፣ እንዳለሙት አልተሳካም፣ ይልቁንስ ለሌላ ዓላማ መጠቀሚያ ኾኗል።

በዚህም “እኛም ተመልሰናል የቀሩትንም መክረን እናመጣቸዋለን” ነው ያለው የቀድሞ ታጣቂው። በቀጣይም ወደ ሥራቸው ተመልሰው ሕዝባቸውን እንደሚያገለግሉ ለሰላምም በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ የቀድሞ ታጣቂዎቹ ተናግረዋል።

ይህ ግጭት “ወንድም በወንድሙ ላይ የሚፈጸመው በራስ ላይ እልቂት” መኾኑን የተረዱት ሌሎች በርካታ ታጣቂዎችም ወደ ሰላም መመለሳቸውን ቀጥለውበል።

✅ይህ የሰላም መንገድ ለአማራ ክልል ሕዝብ እፎይታን የሚሰጥ፣ የሰላም በርን የሚከፍት መልካም ፍኖት ነው። የሕጻናትን ተስፋ የሚመልስ፣ ልጆችን እንዳሻቸው የሚያስቦርቅ፣ የአረጋውያንን እምባ የሚያብስ፣ የእናቶችን ማቅ አስወልቆ ሸማ የሚያስለብስ በመኾኑ ሁሉም ለሰላም እጁን መዘርጋቱ ተስፋ ኾኗል።🕊️👏

እርስዎስ ምን አስተያየት አለዎት? ያካፍሉን👇

#አሚኮ #Peace #Ethiopia🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_14_2019_ዓ_ም

በአሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየኢትዮጵያን ከተሞች ከሌሎች ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ እያደረገ ያለው ዘመናዊው የእድገት እሳቤ !
Next articleሰው ሰራሽ አስተውሎት ​ለጤናው ዘርፍ ተስፋ ወይስ ስጋት?