ሰላም የሰመረባት ባሕር ዳር፦ የጣና ፎረም ድምቀት

35

 

በአንድ ከተማ የሚዘጋጅ አሕጉራዊ እና ዓለማቀፋዊ ፎረም የቱሪዝም ኮንፈረንስን እና የኢኮኖሚ ልማትን ያሳልጣል። ለሆቴሎች መነቃቃት፤ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፤ ለገጽታ ግንባታ እና ለቱሪዝም ተደራሽነት የሚኖረው ሚና የጎላ ነው።

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጠውን የጣና ፎረም ላለፉት 11 ዓመታት በማስተናገድ ደግሞ ባሕር ዳር ከተማ የካበተ ልምድን አግኝታለች። ጣና ፎረም ከከተማዋ አልፎ የክልሉን ገጽታ በመገንባት ረገድ የማይተካ ሚናን እየተወጣ ይገኛል።

በክልሉ የተፈጠረው ሰላም 12ኛውን የጣና ፎረም የሚካፈሉ የአፍሪካ ከፍተኛ መሪዎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የቀድሞ ታዋቂ የአፍሪካ ሰዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የተለያዩ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኞች እና ጥናት እና ምርምር ላይ የሚሳተፉ ምሁራን እንዲገኙ አድርጓል።

12ኛውን የጣና ፎረም ለመካፈል የመጡ ከፍተኛ መሪዎች ከተማዋ በኮሪደር ልማት ልዩ ገጽታን ተጎናጽፋ አግኝተዋታል። በከተማዋ የተገነቡ መሠረተ ልማቶች የሆቴል ኢንቨስትመንቶች ልዩ ገጽታን አጎናጽፈዋታል።

በከተማዋ ያለው ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሰላምን አስፈላጊነት በሚገባ አሳይቷል።

ሰላማዊ እንቅስቃሴ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተጠናቅቆ ዳግም ዓለማቀፍ ጨዋታዎችን እንዲያስተናግድ ዕድል ፈጥሯል።

በከተማዋ እየተስተዋለ የሚገኘው ሁለንተናዊ ለውጥ ዘንድሮም በጣና ፎረም ታጅቧል። በርካታ አሕጉራዊ እና ዓለማቀፋዊ እንግዶች ከጥቅምት 12 ጀምሮ ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል። የጣና ፎረም በውቢቷ ባሕር ዳር በመካሄድ ላይም ይገኛል።

የፎረሙ መካሄድ በአማራ ክልል የተፈጠረውን ሰላም የሚያሳይ፣ የቱሪዝም ኮንፈረንስን የሚያነቃቃ፣ ባለሃብቶች ወደ አካባቢው እንዲመጡ የሚያስችል እና ሌሎች ገጸ በረከቶችን የሚፈጥር ነው።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_14_2019_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ !

Previous articleፈተናን ወደ ዕድል፤ የመገጭ ግድብ የስኬት ጉዞ 🇪🇹
Next articleበአማራ ክልል የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሽልማት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።