በአማራ ክልል የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሽልማት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

35

 

በ2018 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከአማራ ክልል ተፈታኝ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ላመጡት የሽልማት እና የዕውቅና መስጠት መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ መሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር) እንዲኹም ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ በትምህርት ዘመኑ የላቀ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች እንዲኹም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት፣ ዞኖች እና ከተማ አሥተዳደሮች ልዩ ልዩ ሽልማቶች እና ዕውቅና እየተሰጠ ይገኛል።

#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_14_2019_ዓ_ም

✍️ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleሰላም የሰመረባት ባሕር ዳር፦ የጣና ፎረም ድምቀት
Next article“ዘመናዊ የመሬት አሥተዳደር ሥርዓት ብልሹ አሠራርን እና የሙስና ችግርን የሚፈታ ነው” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)