
ኢትዮጵያ በየዘመናቱ በርካታ ፈተናዎች ቢጋረጡባትም፣ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ እና ወደ ዕድል በመቀየር ትላልቅ የልማት ፕሮጄክቶችን በማጠናቀቅ የሕዝቦቿን ተጠቃሚነት እያረጋገጠች ትገኛለች።
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የዚህ የጽናት ውጤት እንደኾነ ሁሉ “ዳግም ሕዳሴ” ይሉ ዘንድ ለምረቃት የበቃው የመገጭ የመስኖ እና የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጄክትም የዚሁ ሀገራዊ የስኬት ጉዞ ሌላኛው ማሳያ ነው።
ይህ ፕሮጀክት ለረጅም ጊዜያት በተለያዩ ምክንያቶች ተስተጓጉሎ እና ዘግይቶ ቆይቷል። ፕሮጄክቱ ለታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ እና ለአካባቢው ማኅበረሰብ የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄ የነበረ ከመኾኑም በላይ ሕዝቡ በጉጉት የጠበቀው ሀገራዊ የልማት ተስፋ ነው።
አሁን ላይ ግድቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ውሳኔ ሰጭነት እና ትኩረት ዳር ሊደርስ ችሏል። ይህ መኾኑም የአካባቢውን ማኅበረሰብ በመስኖ ልማት ተጠቃሚ በማድረግ የምግብ ዋስትናን ያረጋግጣል፤ የታሪካዊቷ ጎንደር ከተማን የቆየ የንጹሕ መጠጥ ውኃ እጥረት በዘላቂነት ይፈታል።
በዓሳ ሃብት ልማት እና ለመዝናኛ አገልግሎት በመዋል ለብዙ ወጣቶችም የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ይታመናል። ይህ ስኬት ኢትዮጵያ የታላላቅ ፕሮጄክቶቿን ፍጻሜ እያፋጠነች እና የሕዝቦቿን ጥያቄዎች እየመለሰች የምታደርገውን የብልጽግና ጉዞ እውን እያደረገች መኾኑንም አመላካች ነው።
የመገጭ ግድብ ለጎንደር ከተማ ሕዝብ የውኃ ጥማት ምላሽ ከመስጠቱ ባሻገር፣ በኢትዮጵያ የግብርና እና የመስኖ ልማት ባሕልም የራሱን ትልቅ አሻራ የሚያስቀምጥ ትልቅ ተግባር ነው።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_14_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ:- ሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
