በወገራ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን ቀጥለዋል።

1
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ ገደብየ እና አካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 25 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
ታጣቂዎቹ የሰላምን አማራጭን የተቀበሉት እስከ ትጥቃቸው ነው። የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች ችግሮች መፍትሔ የሚያገኙት በሰላማዊ መንገድ መኾኑን ተረድተው ሰላምን መምረጣቸውን ተናግረዋል።
የወገራ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሹመት ዋሴ መንግሥት የሰላም አማራጭን ክፍት በማድረግ ግጭት ውስጥ የገቡ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ዕድል እየሰጠ መኾኑን ገልጸዋል።
ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሳቸው ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለአካባቢው ሰላም እና ልማት የሚጠቅም በጎ ተግባርም ነው ብለዋል። ሌሎችም የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የወገራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አይፈራም አያናው ሥልጣን በጉልበት ሳይኾን በምርጫ የሚመጣ መኾኑን ተናግረዋል።
የማንም ተላላኪ ባለመኾን የሰላም ምርጫውን መከተላችሁ የኅብረተሰቡን ዘላቂ ሰላም በማምጣት የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ያግዛል ብለዋል።
ከወገራ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት መሪዎች ሰላምን መምረጥ ለግለሰቦችም ኾነ ለማኅበረሰቡ ያለው ፋይዳ ትልቅ መኾኑን ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበተራራዎች የተከበበችው የሰላም ወደብ፤ የሰው ማዕበል የሚፈስስባት አምባሰል