የኮሪደር ልማት፣ ተኪ ምርት እና “መሶብ” የሐረሪ ክልልን ገጽታ የቀየሩ ስኬቶች

11

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ልዑካን በሐረሪ ክልል የተከናወኑ የኮሪደር ልማት፣ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎችን እና የሞዴል መንደሮች ግንባታን ጎብኝተዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ አስተባባሪ፣ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኀላፊ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል እንደገለጹት ክልሉ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን የማስቀረት ሥራ በስፋት አከናውኗል።

በተለይም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የፖል ምርቶችን ለኮሪደር ልማት በማዋል ከተማዋን ማራኪ ማድረግ መቻሉን በምልከታ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች በአንድ ቦታ የተለያዩ አገልግሎቶችን በማግኘት ጊዜ እና ወጫቸውን እንዲቆጥቡ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

የአካባቢውን ሃብት እና ጥበብ ያቀናጁት የገጠር ሞዴል መንደሮችም ለሌሎች አካባቢዎች በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰዱ መኾናቸውን ገልጸዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ናትናኤል ሚሊዮን የሐረሪ ክልል ጥንታዊ እና ታሪካዊ እሴቶችን በጠበቀ መልኩ ያከናወነው የኮሪደር ልማት እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሊጠናከር የሚገባው አርዓያነት ያለው ተግባር ነው ብለዋል።

በዚህ የምልከታ መርሐ ግብር ላይ የሐረሪ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሮዛ ኡመርን ጨምሮ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

#አሚኮ #ልማት #በሐረሪክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_12_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🕊️ የመንግሥት የሰላም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት።
Next article“ከሱማሊያ እስከ ምጽዋ ጫፍ የቀጣናው የሰላም ጋሻ”👏