🕊️ የመንግሥት የሰላም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት።

29

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) በተለያዩ አጋጣሚዎች “ከጦርነት አሸናፊነት ይልቅ የሰላም አሸናፊነት ይበልጣል፤ ፍላጎታችን በጠረጴዛ ዙሪያ ተነጋግሮ ማሸነፍ ነው” በማለት መንግሥት ለሰላም ያለውን የጸና አቋም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ያጋጠሟትን ውሥብሥብ ፖለቲካዊ እና የጸጥታ ቀውሶች ለመፍታት ከኅይል ይልቅ ሰላማዊ የውይይት አማራጮችን አስቀድማለች።

መንግሥት የትጥቅ ትግልን ከመረጡ ኀይሎች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ለመወያየት ያሳየው ተነሳሽነት ለሰላም የሰጠውን የላቀ ትኩረት ያመላክታል።

የመንግሥት የሰላም ጥረት ትልቁ ተጨባጭ ማሳያ በፌዴራል መንግሥት እና በሕገ ወጡ የሕወሃት ቡድን መካከል ለሁለት ዓመታት ተካሂዶ የነበረውን አውዳሚ ጦርነት ለማስቆም የተከናወነው የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ነበር።

መንግሥት ለዚህ ስምምነት መሳካት ያሳየው ቁርጠኝነት፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲጀመር፣ መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲቋቋሙ፣ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓት እንዲዘረጋ እና የትጥቅ ማስፈታት ሂደት እንዲጀመር በማድረግ በኩል ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

በባህሪው ሰላም የማይፈልገው ሕገ ወጡ ቡድን ግን ስምምነቱን በማፍረሱ ምክንያት የሰላም ሂደቱ ክፉኛ ተፈትኗል። ይህ ሁኔታ የመንግሥት የሰላም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ጦርነትን እንደ ብቸኛ አማራጭ በሚያዩ ታጣቂዎች ዘንድ በቀላሉ መገፋቱን እና ክብደት ማጣቱን በጉልህ የሚያሳይ ነው።

መንግሥት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ያሉ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ያሳየው የሰላም ጽናት ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን አሳይቷል። በኦሮሚያ ክልል ከሸኔ ታጣቂ ቡድን ጋር በታንዛኒያ ተከታታይ የሰላም ንግግሮች ተካሂደዋል።

በአማራ ክልል ከተፈጠረው የጸጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞም የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የሃይማኖት አባቶችን እና ምሁራንን በማሳተፍ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ተደርጓል። እነዚህ መንግሥት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ናቸው።

ባለፉት ዓመታት የታዩት ተጨባጭ ውጤቶች ኢትዮጵያ የቱንም ያህል ውሥብሥብ የኾኑ የጸጥታ ችግሮች ቢገጥሟትም የመጨረሻው ዘላቂ መፍትሔ ሰላማዊ ውይይት መኾኑን አጥብቃ መያዟን የሚያሳዩ ናቸው።

#ቅድሚያሰላም #ኢትዮጵያ🇪🇹 #አሚኮ

#ባሕር_ዳር #መሥከረም _12_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleኢትዮጵያ አትወድቅም፤ የወደቁትን ታነሳለች እንጂ።
Next articleየኮሪደር ልማት፣ ተኪ ምርት እና “መሶብ” የሐረሪ ክልልን ገጽታ የቀየሩ ስኬቶች