
በአማራ ክልል ከሰሞኑ በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው። ዛሬ ደግሞ በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የፋርጣ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ ሃምሳ አለቃ ማሩ አድማስ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን በማጠናከር እና ከታጣቁ አካላት ጋር ቀርቦ በመነጋገር ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ትናንት እና ዛሬ 32 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበላቸውንም ገልጸዋል። በቀጣይ በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን አንስተዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች ከአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላት ጋር በመሥራት ዳግም ሕዝብ አንበድልም በማለት የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን ገልጸዋል።
ማኅበረሰቡ ሰላምን ለማጽናት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መኾኑንም አንስተዋል።
#አሚኮ #ሰላም #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_11_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
