ጽናት ኢትዮጵያን ከፈተና አሻግሯል ።

0

 

በከሚሴ ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ የጸጥታ መዋቅሮች እና የከተማዋ ነዋሪዎች የጽናት ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩ ነው።

የጸጥታ አባላቱ ለአሚኮ በሰጡት አስተያየት በውስጥ እና በውጭ ኃይሎች የሚገጥሙ የጸጥታ ስጋቶችን በመቀናጀት በጽናት የመከተ የጸጥታ መዋቅር መኖሩን ገልጸዋል። ወደፊትም ለሀገር ሉዓላዊነት በጽናት እንደሚታገሉ አረጋግጠዋል።

የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም የጸጥታ መዋቅሩ ሀገራዊ ጽናትን በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የገጠሟትን የጸጥታ እና የፖለቲካ ፈተናዎች በጽናት በመቆም የተሻገረች መኾኗን ነው የገለጹት። ይህን ወደፊትም የምታስቀጥል እንደኾነች አስረድተዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ አወል እንድሪስ የሀገራችን የጸጥታ መዋቅሮች ለፈተናዎች የማይበገሩ እና በጽናት ለያዙት አላማ እስከመጨረሻው የሚዋደቁ እንደኾኑ ተናግረዋል።

የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ማሸነፍ የሚቻለው ሕዝብ እና የጸጥታ መዋቅሩ በቅንጅት ሢሠሩ በመኾኑ መላው ማኅበረሰብ ከጸጥታ ኃይሉ ጎን መኾን እንዳለበትም አንስተዋል።

#ከሚሴ #ጳጉሜን_03_2018_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየጸጥታ ኃይሉ የጸረ ሰላም ኃይሎችን ምኞት በከንቱ ያስቀረ የሀገር መከታ ነው።
Next articleበአማራ ክልል ምን ያክል የዲጂታል መፍትሔዎች ለምተው ለአገልግሎት ዋሉ ?