“የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መጠበቅ የትውልዱ አደራ ነው”

9
የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማስተዋወቅ ታላሚ ያደረገ የአረጋውያን የከተማ የቱሪዝም መዳረሻዎች ጉብኝት አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በማብቃት እና በመቆጣጠር በከተማዋ የሚገኙትን መዳረሻዎች የማልማት እና የመንከባከብ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል። ይህም ከተማዋ ከቱሪዝም ዘርፉ ተጠቃሚ እንድትኾን ያስችላል።
የዚህ ሥራ አንዱ አካል የኾነው የአረጋውያን የከተማ ቱሪዝም መዳረሻዎች ጉብኝት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ተካሂዷል።
በጉብኝቱ ወቅት አሚኮ ያነጋገራቸው አረጋውያን በከተማዋ የተሠሩ የልማት ሥራዎች አመርቂ ለውጥ አመላካች እና ታሪክን ነጋሪ በመኾናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ትውልዱም ይህን ቅርስ መጠበቅ ታሪኩንም ማስቀጠል እና ልማቱን በመደገፍ መተባበር እንዳለበትም አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ዳይሬክተር አማኑኤል ባቡ የከተማዋን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማጠናከር በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን ገልጸዋል።
ዛሬ በአረጋውያን የተጎበኙ የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክቶች በፍጥነት እና በጥራት መሠራታቸውን እና የከተማዋ ዕድገት ላይ ለውጥ ያመጡ መኾናቸውን አስገንዝበዋል።
ወደፊትም የኢትዮጵያን ከፍታ ያረጋገጠ ሥራ መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።
ዘጋቢ: ሰለሞን አሰፌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአብሮነት መኖርን ለአማኞች በማሳየት ዕምነትን በተግባር ያሳየ ተቋም ነው” የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Next articleያልተነጣጠሉት ሥጋ እና ነፍስ የሰላም እጦት ዋጋ እና የኢኮኖሚ ማገገም ተስፋ።