
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
በጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች እና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ “የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማትጉባኤ ዕምነትን በተግባር በማሳየት ለሀገር ሰላም እና ለአብሮነት የሠራ ጉባኤ ነው”ብለዋል።
የሃይማኖት ተቋማት የሰላም መሠረት ናቸው፤ ጉባኤው በ15 ዓመታት ጉዞው የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን ከአማኞች ጋር በመኾን በፀሎት እና በተግባቦት መፍትሔ እንዲያገኙ በማድረግ ኀላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል ነው ያሉት።
በቀጣይም ጉባኤው ለሀገር እና ለሕዝብ ጥቅም እንዲሠራም አሳስበዋል።
ዘጋቢ: ራሔል ደምሰው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
