ለግንዛቤ! ከዲጅታል ይዘት ፈጠራ ከሚገኝ ገቢ ስለሚከፈል ግብር፦

8
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ንዑስ አንቀጽ 29 መሠረት ከዲጅታል ይዘት ፈጠራ ከሚገኝ ገቢ ግብር እንዲከፈልበት መደረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አሳውቋል።
✍️ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ምን ማለት ነው?
አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎቶችን፣ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን፣ የድምጽ ማስተላለፊያ (ፖድካስት) አገልግሎቶችን እና የቀጥታ ስርጭት መድረኮችን ጨምሮ በኦንላይን መድረኮች ላይ ዲጂታል ይዘትን በመፍጠር እና በማሰራጨት የሚያገኘው ማንኛውም የገንዘብ ወይም በአይነት የሚገኝ ገቢን እንደማያጠቃልል ተጠቅሷል።
✍️የሚያካትተታቸው ገቢዎችስ?
#ማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖች፣
#የምርት ስም ስምምነቶች እና ድጋፎች፣
#የአጋርነት ግብይት እና የምርት ምደባዎች፣
#የደጋፊዎች አስተዋጽኦ፣ የገንዘብ ስጦታዎች ወይም የብዙኅን የገንዘብ ማሰባሰብ(ክራውድ ፈንዲንግ)፣
#የአባልነት ክፍያዎች፣
#የዲጂታል ወይም የአካላዊ ሸቀጦች ሽያጭ፣
#ለማስተዋወቂያ እንቅስቃሴ ምትክ የተገኙ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች እና
#ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ሌሎች ክፍያዎችን ያጠቃልላል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የብሔረሰቦች ቀን የሕዝቦችን መተዋወቅ እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታን በተግባር የምናሳይበት ታሪካዊ መድረክ ነው” አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር
Next article“የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአብሮነት መኖርን ለአማኞች በማሳየት ዕምነትን በተግባር ያሳየ ተቋም ነው” የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ