ታሪካዊ መረጃ ሳይጠቀም አደጋዎችን የሚተነብየው ቴክኖሎጂ!

6
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ተመራማሪዎች ታሪካዊ መረጃዎችን እንደ ዋቢ ሳይጠቀሙ ከዚህ ቀደም ታይተው የማይታወቁ የአየር ኹኔታዎችን አስቀድሞ መተንበይ የሚያስችል አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አስተዋውቀዋል፡፡
ይህ ቴክኖሎጂ ከነባር የአየር ኹኔታ ሞዴሎች በተለየ መልኩ ቀደም ሲል ከተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች መረጃ ላይ ጥገኛ ሳይኾን በስታቲስቲክስ ስሌት ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን መተንበይ ያስችላል ተብሏል።
ሞዴሉ የክስተቶችን ድግግሞሽ የሚያሳዩ የስታቲስቲክስ መረጃዎችን እና የቦታ ሥርጭት ካርታዎችን በማጣመር ይሠራል። ለአብነት በኒውዮርክ ከተማ በታሪክ ከተመዘገበው 200 ሚሊ ሜትር የዝናብ መጠን በላይ የኾነን የ300 ሚሊ ሜትር ማዕበል ሥጋት በትክክል ማሳየት ችሏል።
ይህ አዲስ ግኝት ከተሞች በ100 ዓመት አንዴ ሊከሰቱ የሚችሉ የከፋ አደጋዎችን አስቀድመው እንዲገምቱ ያስችላል።
ይህም የመሰረተ ልማት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የአደጋ ጊዜ ዝግጅታቸውን እንዲፈትሹ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያሳያል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleለጋራ ሰላም በጋራ መቆም በመቻሉ ውጤት ተገኝቷል።
Next articleየሰላም ችግኝን ማን ይትከል?