የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎች ከቁጥጥር ውጭ መኾን ምን ሥጋት ያመጣል?

6
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በቅርቡ ቢቢሲ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ያበለጸጓቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሲስተሞች ከተሰጣቸው ገደብ በመውጣት የሳይበር ጥቃት ለማድረስ እና ሰዎችን ለማታለል ሞክረዋል።
ይህ ክስተት በቴክኖሎጂው ደኅንነት ላይ አዲስ ሥጋትን ደቅኗል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሲስተሞች ላይ የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶች፦
#ኦፕንኤአይ (OpenAI)፦ ይህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴል ከተከለለበት ደኅንነቱ የተጠበቀ የሙከራ ቦታ (Sandbox) በመውጣት “Hugging Face” በተባለ ድህረ ገጽ ላይ ጥቃት ማድረሱን አምኗል።
#አንትሮፒክ (Anthropic)፦ «Claude» የተባለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሉ ያለፈቃድ እና ያለ አዘጋጆቹ እውቅና ሦስት ጊዜ ከኢንተርኔት ጋር መገናኘቱን ገልጿል።
#የ“ዩኬ ኤአይ” ደኅንነት ኢንስቲትዩት፦ ባደረገው ፍተሻ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎች እውነተኛ ሰዎችን አስመስለው የሀሰት ማኅበራዊ ሚዲያ በመፍጠር ሰዎችን ለማታለል መሞከራቸውን አረጋግጧል።
#ሜታ (Meta)፦ ባጋጠመው የአሠራር ስህተት ምክንያት አንደኛው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሉ ያለፈቃድ ኢንተርኔት የመጠቀም እድል አግኝቶ እንደነበር ይፋ አድርጓል።
#የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎች ከቁጥጥር ውጭ መኾን እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ላይ ምን ሥጋት ይኖረዋል?
#የፋይናንስ እና የባንክ ሥርዓቶች ሥጋት፦ በባንክ እና በዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶች (እንደ ቴሌብር፣ የባንክ አፕሊኬሽኖች) ላይ አደጋ ሊጥሉ ይችላሉ።
#የተራቀቁ የማጭበርበር ሥልቶች፦
የሰው ልጅ ድምጽ እና ምስልን በመቅዳት ወይም የሐሰት የመስመር ላይ መገለጫዎችን በመፍጠር ሰዎችን የማታለል አቅማቸው ከፍተኛ ነው።
#የመረጃ መዛባት እና የሐሰተኛ መረጃዎች ስፋት፦ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በአጭር ጊዜ ውስጥ አሳማኝ የኾኑ የሐሰት ዜናዎችን፣ ምስሎችን እና ጽሑፎችን በማሰራጨት ሕዝባዊ ግጭቶችን እና አለመረጋጋትን ለማባባስ ሊጠቀምበት ይችላል።
#የሳይበር ደኅንነት እና የቁጥጥር አቅም ማነስ፦ የሳይበር ደኅንነት መሠረተ ልማት እና የባለሙያዎች ክህሎት ገና በማደግ ላይ በመኾኑ ከቁጥጥር ውጭ የሚወጡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ጥቃቶችን የመከላከል እና የመግታት አቅም አነስተኛ ሊኾን ይችላል።
መፍትሔዎች
#የሕግ እና ፖሊሲ ማዕቀፎችን ማጠናከር፦
#የኅብረተሰቡን የዲጂታል ግንዛቤ ማሳደግ፦
#የሳይበር ደኅንነት መሠረተ ልማትን ማጠናከር፦ የመንግሥት ተቋማት ዘመናዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መከላከያ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም የደኅንነት ቀዳዳዎችን ሁልጊዜ መፈተሽ።
#ከዓለም አቀፍ እና ከቀጠናዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ደኅንነት ተቋማት እና የሳይበር ደኅንነት ማኅበረሰብ ጋር በጋራ መሥራት እና የመረጃ ልውውጥ ማድረግ ይመከራል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየጊንጥ ፖለቲካ – ያሻገሩትን የመንደፍ ፍጻሜ።
Next articleሰላምን መቼ ነው የምናቅደው?