ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለታዳጊዎች ዕድል ወይስ?

8
ባሕር ዳር: ነሐሴ 18/12/18 ዓ.ም (አሚኮ) የዲጂታል ቴክኖሎጂ መስፋፋት የሕጻናትን የመማር፣ የመጫወት እና የማኅበራዊ ግንኙነት ልምድ መሠረታዊ በኾነ መንገድ እየቀየረው ይገኛል።
የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መብቶች ፈንድ (ዩኒሴፍ) የቴክኖሎጂውን መልካም እድሎች እና ደኅንነትን የሚፈታተኑ ሥጋቶችን አስቀምጧል።
​መረጃው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሕጻናትን ሕይወት፣ ትምህርት እና የአዕምሮ ደኅንነት በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች መስፋፋት ምክንያት እንዴት እየተቀየረ እንደኾነ በዝርዝር ያብራራል።
ቴክኖሎጂው ለሕፃናት የሚያስገኛቸውን አወንታዊ እድሎች፣ የሚያጋጥሟቸውን አሉታዊ ተጽዕኖ እና አደጋዎች ይዳስሳል።
✍️አዎንታዊ ተጽዕኖዎች
#ኢንተርኔት ለሕፃናት የመጫወቻ፣ ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር የመገናኛ፣ የመማሪያ እንዲኹም ለወደፊት ህይወታቸው የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን ማዳበሪያ መሠረታዊ ፍላጎት ኾኗል።
#ሕጻናት በሰላም እና በደኅነት የሚጫወቱበት፣ የሚማሩበት እና ራሳቸውን የሚያሳድጉበት እድል ይሰጣል።
✍️አሉታዊ ተጽዕኖዎች
#በአፍሪካ እና በኤስያ አህጉራት የሚኖሩ ሕጻናት የኢንተርኔት ተደራሽነት ማጣታቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የዲጂታል ክህሎት ልማት ውድድር ተቀላቅለው የመጠቀም እድላቸውን አጥብቦታል።
#ከፍተኛ የዲጂታል ተደራሽነት ባላቸው ሀገራት በወጣቶች መካከል የአዕምሮ ጤና ችግሮች እየጨመሩ መምጣታቸው ይታያል፤ የስማርት ፎን፣ የማኅበራዊ ሚዲያ እና የኦንላይን ጨዋታ ተጽዕኖም ከፍተኛ ፈተና ኾኗል።
#ንግድ ነክ ኩባንያዎች እና ባለድርሻ አካላት ትርፋማ የዲጂታል ዓለምን ለመገንባት በሚያደርጉት ሩጫ የሕፃናት ድምጽ እና የዕለት ከእለት ተሞክሮ ሳይደመጥ ይቀራል።
#የልጆች የዲጂታል አጠቃቀም በክህሎታቸው እና በአእምሮ ጤናቸው ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በተመለከተ ያለው ግንዛቤ አኹንም የተወሰነ ነው።
​በመኾኑም ሕጻናት በሰላም እና በደኅነት የሚጫወቱበት፣ የሚማሩበት እና ራሳቸውን የሚያደጉበት የዲጂታል ምህዳር በመፍጠር ከቴክኖሎጂው በጎ ጎን እንዲጠቀሙ እና ከአደጋዎች እንዲጠበቁ ማድረግ ይገባል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሚስ ሻደይ የቁንጅና ውድድር እየተካሄደ ነው።
Next articleግንድ እና ወርቅ ይዞ ከመዞር የታቀበው ወንዝ ዛሬስ?