ሚስ ሻደይ የቁንጅና ውድድር እየተካሄደ ነው።

16
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር እየተከበረ የሚገኘው የሻደይ በዓል ጨዋታ በተለያዩ ትርዒቶች ታጅቦ በድምቀት መከበሩን ቀጥሏል።
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሚስ ሻደይ የቁንጅና ውድድር መካሄድም ጀምሯል።
የዋግ ኽምራን ባሕላዊ አለባበስ እና አጊያጊያጥ በማሣየት እና የዋግ ኽምራን የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ በሚደረገው የሚስ ሻደይ የቁንጅና ውድድር በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከሁለቱ ከተማ አሥተዳደሮች እና ከ7 ወረዳዎች የተውጣጡ የቁንጅና ተወዳዳሪዎች ቁንጅናቸውን እያሥተዋወቁ ይገኛሉ።
የሚስ ሻደይ አሸናፊም በቀጣይ የዋግ ኽምራ የባሕል አምባሳደር በመኾን የአካባቢውን ባሕል እና የቱሪዝም ሃብቶችን የማስተዋወቅ ኀላፊነት የሚሰጣት ይኾናል።
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ኢትዮጵያ በሀገራዊ ምክክር ከኃይል አዙሪት ወደ ሐሳብ ልዕልና ተሸጋግራለች” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት