
ሕገወጡ ህወሃት በሥልጣን ላይ በቆየበት ዘመን የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች በቋንቋቸው እንዳይናገሩ፤ በባሕላቸው እንዳያጌጡ፤ የአማራነት መገለጫ የኾኑ አልባሳትን እንዳይጠቀሙ ሲያደርግ ቆይቷል።
ሕገወጡ ቡድን በዚህ ብቻ አላቆመ፤ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸም፤ አማራዎችን በማሳደድ እና በማፈናቀል የአካባቢውን ሥነ ምህዳር ለመቀየር ጥረት አድርጓል።
የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማኅበር ዋና ሥራ አሥኪያጅ ዶክተር ገሠሠው ወንድም፣ ሕገ ወጡ ህወሃት በ27 ዓመት ቆይታው በወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ሕዝብ ላይ በደል ሲፈጽም እንደነበር አንስተዋል።
የሃይማኖት አባቶች፣ ታሪክ አዋቂዎች፤ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን በባዶ ስድስት ካምፕ እንዲታሠሩ በማድረግ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ነው ያሉት። የትግራይ ተወላጆችን በወልቃይት ምድር በማስፈር በሺዎች የሚቆጠሩ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ተወላጆች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል ብለዋል።
ለማንነታቸው የሚታገሉ፤ አማራ ነን የሚሉ ነዋሪዎችን በመጨፍጨፍ በባዶ ስድስት እና በሌሎች አካባቢዎች በጅምላ ቀብሯል። ለዚህ ማሳያ ደግሞ በ2014 ዓ.ም የጎንደር ዩኒቨርስቲ ባደረገው ጥናት “ገሃነም” በሚባል ቦታ የጅምላ መቃብር ማግኘቱን ነው።
ሕገወጡ ቡድን በኢትዮጵያዊያን ትግል ከሥልጣን ከተወገደ በኋላ በ2013 ዓ.ም በከፈተው ጦርነት በርካታ ንጹሐንን በማይካድራ ከተማ ጨፍጭፏል።
ሁሉንም የራሱ ማድረግ፤ ኢትዮጵያን በብቸኝነት መግዛት የሚፈልገው ይህ ቡድን በወልቃይት ላይ የፈጸመውን ግፍ መርሳት ከቶ አይቻልም።
የሕገ ወጡ ህወሃት አሁናዊ የጥፋት ጥምረት
እኔ ያልገዛኋት ሀገር ትፍረስ ብሎ የሚንቀሳቀሰው ሕገ ወጡ ቡድን ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እና ከውስጥ ታጣቂዎች ጋር ጥምረት ፈጥሮ ለጥፋት እየሠራ ይገኛል።
በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችም የአማራ ሕዝብን የማንነት እና የወሰን ጉዳይ ቀይ መሥመርን በማለፍ ከሕገወጡ ህወሃት ቡድን ጋር ለዳግም ጥፋት ተጣምረዋል።
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ከቶ እንዴት ወልቃይትን ረሱ? የገሃነምን፣ የባዶ ስድስትን፣ የማይካድራ ጭፍጨፋን እንዴትስ ዘነጉ? “ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ” ብለው በ2008 ዓ.ም ሕይወታቸውን የገበሩ የወጣቶች መስዋዕትነት እንዴት ረሱ የብዙዎች ጥያቄ ኾኗል። በማያስማማቸው፤ በማያግባባቸው በወልቃይት ጉዳይ ከቶ እንዴት ተግባቡ? የአማራ ሕዝብ የደም ዋጋ የገበረበትን የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ከቶ እንዴትስ ዘነጉ? የሕዝብን ጥያቄ ለማስመለስ ጫካ ገባሁ የሚል ታጣቂ ከአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላት ጋር መሥራት ሕዝብን መካድ አይሆንም ወይ? የሚሉት ጥያቄዎች የታጣቂ ኀይሎችን የተሳሳተ አካሄድ ያመላክታል።
የጥፋት ጥምረቱ የጋራ ጠላት እንጅ የጋራ ሀገራዊ ዓላማ የለውም። የሕዝብን ድምጽ መስማት፤ ከታሪካዊ የጥፋት ጥምረት መራቅ፤ የሰላምን አማራጭ መቀበል እና ለሕዝብ ሰላም እና እፎይታ መስጠት ከሁሉም ታጣቂዎች የሚጠበቅ ቀዳሚ ተግባር ነው።
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀመንበር አረጋዊ በርሄ (ዶ.ር) ሻዕቢያ እና ሕገወጡ የህወሃት ቡድን የግብጽን ዓላማ ለማስፈጸም እየሠሩ መኾኑን ገልጸዋል። ሉም ኢትዮጵያ በመተባበር ሀገሩን እና መብቱን ሊያስከብር ይገባል ነው ያሉት። የትግራይ እናቶች ልጆቻችንን አትወስዱም፤ ለጦርነት የምንሰጠው ስንቅ የለንም በማለት፤ ወጣቶች ደግሞ አፈና ይብቃ እያሉ ሕገወጡን ቡድን እየተቃወሙ መኾኑን ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
