ከ562 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያስገኘው ጸጋ ምንድን ነው?

18
የአማራ ክልል የግብርናው ምርት ለኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ክልሉ ከፍጆታ ምርቶች በተጨማሪ ለውጭ ገበያ እና ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች የግብዓት አቅርቦት ትልቅ አቅም እንዳለው መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በተለይም በቅባት እና በጥራጥሬ ምርቶች ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት እና ለውጭ ገበያ በመላክ በኩል ከሀገሪቱ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኀላፊ አትክልት አሳቤ ይገልጻሉ።
በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ከ5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የቅባት እና ጥራጥሬ ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሉን ተናግረዋል። ከዚህም ከ562 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለክልሉ አስገኝተዋል ነው ያሉት።
እንደ ምክትል ኀላፊዋ ማብራሪያ ከቅባት እህሎች መካከል ሰሊጥ እንዲኹም ከጥራጥሬ ደግሞ አኩሪ አተር በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው። 🌾
🏭በተለይም አኩሪ አተርን ከውጭ ገበያ አቅርቦት በተጨማሪ በክልሉ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎችም በስፋት ለግብዓትነት እየዋለ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ክልሉ ካለው ከፍተኛ የምርት አቅም አንጻር ግን ከዘርፉ የውጭ ገበያ ተጠቃሚነቱ አሁንም አነስተኛ መኾኑን ያብራራሉ።
⚠️ለገበያ ተጠቃሚነቱ አነስተኛ መኾን የተነሱ ምክንያቶች፡
📌 በምርት አሰባሰብ ወቅት የሚከሰት ብክነት
📌 በወቅቱ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ያለማምጣት ችግር
📌 ደረጃቸውን የጠበቁ የገበያ ማዕከላት በበቂ ደረጃ አለመኖር
📌የሕገ ወጥ ንግድ እና የጸጥታ ችግሮችን ምክትል ኀላፊዋ በአብነት አንስተዋል።
🛠️ችግሩን ለመቅረፍ እየተወሰዱ ያሉ የመፍትሄ እርምጃዎች:-
✅ የገበያ መሠረተ ልማቶችን ደረጃቸውን የማሻሻል
✅ የኮንትሮባንድ ንግድን በግብረ ኃይል የመቆጣጠር
✅ ከአምራቾች፣ ከላኪዎች እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር የተቀናጀ የመረጃ ትስስር ስርዓት መዘርጋት ቢሮው በትኩረት ይዞ እየሠራባቸው እንደሚገኙ አመላክተዋል።
✅ የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ በኮንትራት ፋርሚንግ ስርዓት አርሶ አደሮችን እና ባለሃብቶችን የማስተሳስር አሠራሮችን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ ጠቁመዋል።
✍️ዘጋቢ:-አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየሕዝብን ስቃይ መካድ አይሆንም ወይ?
Next article“ኢትዮጵያ በሀገራዊ ምክክር ከኃይል አዙሪት ወደ ሐሳብ ልዕልና ተሸጋግራለች” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት