“ከ20 ሺህ በላይ ዜጎችን የመኖሪያ ቤት ቦታ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል” አቶ ጎሹ እንዳላማው

21
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት እያካሄደ ነው።
የባሕር ዳር የከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው በ2018 በጀት ዓመት መጀመሪያ ፈተናዎች የነበሩበት ቢሆንም የክልሉን የአሻጋሪ እድገት እና ዘላቂ የልማት እቅድ መሠረት በማድረግ እና የ5 ዓመቱን ስትራቴጂክ እቅድ መሠረት ተደርጎ ሥራው መጀመሩ አውስተዋል። በተለይም ከተማዋ የተሻለ ሰላም የሰፈነባት፣ ልማቷ የተረጋገጠ፣ ፈጣን ልማት የሚታይባት ከተማ እንድትኾን ከሕዝቡ ጋር መሠራቱን ገልጸዋል።በዚህም ሰላም እንዲጠበቅ ተደርጓል ብለዋል። ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሕዝብ ጋር በቅንጅት በመሥራት በሰላማዊ ምርጫ ተከናውኗል ነው ያሉት።
የባሕር ዳር ኮሪደር ልማት እና የጣና ልማት የባሕር ዳርን ከፍታ ያረጋገጠ፣ የቱሪዝም ከተማነቷን ተወዳዳሪ እና ከፍ ያደረገ ሥራ የተሠራበት ነው ብለዋል። በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎች ዘርፎችም ውጤታማ ተግባራት ተከናውኗል ነው ያሉት። በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራም ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ብለዋል።
የከተማውን ልማት ሊያረጋገጥ የሚያስችል ገቢ ከ9 ነጥብ 25 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ነው ያሉት። በበጀት ዓመቱ የፓርቲ እና የመንግስት ሥኬታማ ሥራዎች ተከናውኗል ብለዋል። የታቀደው መፈፀሙን አንስተዋል። በተለይም የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታታት በተደገው ቁርጠኛ ተግባርም በከተማው ከ20 ሺህ በላይ ዜጎች የመኖሪያ ቤት ቦታ ባለቤት ማድረግ መቻሉን ነው የገለፁት።
በዓመቱ በርካታ የልማት ተግባራት ተከናውኗል ነው ያሉት።ይህ ዓመት የስኬት ፤ የድል ዓመት ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የታዩ ክፍቶችን በማስተካከል ይህንን ድል አጠናክሮ መቀጠል እና ከዚህ በላይ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
በሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleያልተጋበዙ የዕቃ አውራጆች ወከባ ሕገ ወጥ ነው።
Next articleየሕገ-ወጡ ቡድን አዲስ ሴራ