
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት በርካታ መረጃዎችን በፍጥነት ማግኘት ይቻላል። ነገር ግን ከዚሁ ጋር ተይዞ ከሚመጣው ሀሰተኛ መረጃ (Fake News) ጋር መታገል የወቅቱ ትልቅ ፈተና ኾኗል።
መረጃ እንዴት አሳሳች ኾኖ ይሠራጫል?
ሀሰት መኾኑ እየታወቀ ሰዎችን ለማታለል በታቀደ እና ኾን ተብሎ የሚሠራጭ ሀሰተኛ መረጃ ነው።
መረጃው የተሳሳተ ኾኖ የሚያሠራጨው አካል ግን እውነት መስሎት ወይም ትክክል መኾኑን አምኖበት (ያለ ተንኮል ዓላማ) የሚያሠራጨው መረጃ ነው።
መረጃውን ለመግለጥ የተፈለገበት ዋና ዓላማ ደግሞ በአንድ ግለሰብ፣ ድርጅት ወይም ሀገር ላይ ኾን ብሎ ጉዳት ለማድረስ ተብሎ የሚሠራጭ ነው።
#የምያንማር ተሞክሮ (የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ) እ.ኤ.አ. በ2017 በምያንማር በተከሰተው ቀውስ ላይ ጥልቅ ምርመራ ያካሄዱት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች የፌስቡክ ማኅበራዊ ሚዲያ በሀገሪቱ የጥላቻ ንግግር እንዲዛመት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ይፋ አድርገዋል።
በማኅበራዊ ሚዲያ በተሠራጩ የጥላቻ ንግግሮች ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ተገድለዋል፤ መንደሮች ተቃጥለዋል፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ተፈናቅለዋል።
#የደቡብ አፍሪካ ተሞክሮ፦ በደቡብ አፍሪካ የተዛመቱ ሀሰተኛ መረጃዎች በውጭ ዜጎች ላይ የጥላቻ ማዕበል ማስከተላቸውን የቪኦኤ (VOA) እንግሊዘኛ ክፍል ዘግቧል። የመረጃ ማረጋገጫ ተቋም የኾነው አፍሪካ ቼክ (Africa Check) እንዳመለከተው ደግሞ የስደተኞች ቁጥር ተጋንኖ ቀርቧል።
የውጭ ዜጎች የሀገሪቱን የሥራ እድል ሙሉ በሙሉ ወስደዋል እንዲኹም የእስር ቤቶች አብዛኞቹ እስረኞች የውጭ ዜጎች ናቸው የሚሉ ያለበቂ ማስረጃ የተሠራጩ ወሬዎች ጥቃቱ እንዲባባስ አድርጎታል።
በዚህም ምክንያት የመንጋ ጥቃቶች ተቀስቅሰው የብዙ ስደተኞች ሱቆች ተዘርፈዋል፣ ተቃጥለዋል። ስደተኞች ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገድደዋል። ሀገሪቱ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አበላሽቶታል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
