በደብረ ታቦር ከተማ የመስቀል በዓል ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

9
በደብረ ታቦር ከተማ የመስቀል በዓልን ሃይማኖታዊ እና ቱባ ባሕላዊ እሴቶችን ጠብቆ፣ በይቅርታ አና በአብሮነት በድምቀት ለማክበር ወጣቶች የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ።
የደብረታቦር ከተማ ነዋሪ ወጣቶች እንደተናገሩት ወጣቶቹ የመስቀል አደባባይን ከማጽዳት ባለፈ ሰዎችን የማስታረቅ ሥራ እየሠሩ ነው።
በዓሉ በዩኔስኮ የተመዘገበ የማይዳሰስ የዓለም ቅርስ በመኾኑ ይዘቱ ሳይበረዝ ለቀጣይ ትውልድ ለማሻገር እየተጉ መኾናቸውንም ገልጸዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ተወካይ ኀላፊ ታደሰ ቢያድጌ ወጣቶቹን በማስተባበር የበዓሉን ቦታ የማጽዳት እና የጸጥታ ሥራዎች እየተከናወኑ መኾናቸውን ገልጸዋል።
በተለይም ወጣቶች ጥል ያላቸውን ሰዎች ለማስታረቅ የሚያደርጉት ጥረት ለሌሎችም በጎ አርዓያ የሚኾን ተግባር መኾኑን አብራርተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleለአባላቱ ደስታን የፈጠረው የመዋቅር ምላሽና አሁንም ያልተመለሰው የተዋረድ ምክር ቤቶች ምርጫ ጉዳይ።