በዓለ ደብረ ታቦር በደብረ ታቦር

4

 

የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በደብረታቦር ከተማ ተከብሯል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት የደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አሥተዳዳሪ መላከ ታቦር ዘወዱ መንግሥቱ በዓሉ ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት መከበሩን ገልጸዋል። በበዓሉ ወቅት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች በማገዝ አብሮ የመኖር እና የመረዳዳት ባሕላዊ እሴትን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ አለበል ደመላሽ የቡሄ በዓል አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ጠቁመዋል። በዓሉን የቱሪስት መስህብ ለማድረግ ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ሰፊ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ወጣቶች ባሕላቸውን የመጠበቅ እና ታሪካቸውን ጠንቅቀው የማወቅ ኀላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን
ኅብረተሰቡ ብርሃን የተገለጠበትን የቡሄ በዓል ሲያከብር ለአካባቢው ሰላም፣ ልማት እና ሁለንተናዊ ዕድገት ዘብ በመቆም እና የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊኾን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የደብረታቦር (ቡሄ) በዓል ፍቅርን እና አንድነትን በማጽናት ረገድ ታላቅ መንፈሳዊ ጥቅም እንዳለው ተናግረዋል። ኅብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

#አሚኮ #ቡሄ #ደብረታቦር🇪🇹

#ደብረ_ታቦር #ነሐሴ_13_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፡- ተክለብርሃን ፈንታ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበሕዝብ ስም እየማሉ የሕዝብን ሰላም መንሳት ይብቃ
Next articleስሙን የወረስሽ፣ ግብሩን የጠበቅሽ – ደብረ ታቦር