
በአማራ ክልል ለረጅም ጊዜ የዘለቀው የሰላም እጦት የክልሉን ሕዝብ ለዘርፈ ብዙ ቀውስ ዳርጎታል። ግጭቱ በሕዝብ ደኅንነት፣ በማኅበራዊ መስተጋብር እና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አደጋ ጥሏል።
⚠️ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፣ የሕክምና አገልግሎት እንዲስተጓጎል ምክንያት ኾኗል፤ እናቶች፣ ሕጻናት እና አረጋውያን ለከፋ ችግር ተዳርገዋል።
በየወቅቱ በሚከሰቱ የተኩስ ልውውጦች የበርካታ ንጹሐን ሕይወት እንዲቀጠፍ ምክንያት ኾኗል። በግጭቱ የልጆቻቸውን ሕይወት የተነጠቁት እናቶች ነጭ ልብሳቸውን አውልቀው ማቅ እንዲለብሱ አድርጓል።
የሕግ የበላይነት እንዳይከበር፣ ፍትሕ እንዳይሰፍን፣ ሰው ወጥቶ እንዳይገባ፣ ሠርቶ እንዳይበላ፣ አርሶ አደሮች በአግባቡ እንዳያመርቱ መሰናክል ኾኗል። 🚫
በየአካባቢው ሕገወጥ ቡድኖች እና ዘራፊ ወንበዴዎች ተስፋፍተው ሕዝቡ እየተዘረፈ፣ ዜጎች እየታፈኑ ገንዘብ ይጠየቅባቸዋል።
🛑ግጭቱ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና መፈናቀል የንጹሐን ሕይወት ማለፍ፣ አካል ጉዳተኝነት፣ መፈናቀል እና የሥነ-ልቦና ቀውስ እንዲባባስ አድርጎታል። የመሰረተ ልማት ውድመትም የክልሉን ኢኮኖሚ ወደ ኋላ መልሶታል። በትውልድ ላይም ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
በተለያዩ አካባቢዎች አስተያየታቸውን የሰጡት የክልሉ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ግጭት ይብቃ ሰላማዊ አማራጭ ይቅደም የሚል ድምጾችንም እያሰሙ ነው። ግጭት እና ጦርነት ሰልችቶናል በማለትም እየተማጸኑ ይገኛሉ።
መንግሥት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። የተዘረጋውን የሰላም አማራጭ በመጠቀም በርካታ ታጣቂዎችም ወደ ሰላም መንገድ ተመልሰዋል፤ እየተመለሱ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት በክልሉ አንጻራዊ ሰላም ለተፈጥሯል። ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ግን አሁን ብዙ ሥራ ይጠበቃል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተለያየ ወቅት እንደተናገሩት በክልሉ የዘለቀው ግጭት ሕዝቡን ለከፋ ስቃይ እየዳረገው ይገኛል።
የታጠቁ ኀይሎች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ ሲገባቸው ባልተገባ መንገድ የሕዝቡን ስቃይ እና መከራ እያራዘሙት መኾኑን አንስተዋል።
እነዚህ ኀይሎች በአማራ ሕዝብ ስም እየማሉ እና እያደናገሩ ከአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተባብረው የሕዝቡን ሕይወት እና ንብረት አደጋ ላይ ጥለውታል ነው ያሉት። ይህም በቃ ሊባል እንደሚገባ አሳስበዋል።
🕊️በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁሉም በየአካባቢው ሰላሙን በመጠበቅ በኩል ባለቤት ሊኾን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
#AMECO #Peace #Ethiopia
#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_13_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
