ታላቅ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል።

12
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገብረ ሥላሴ የምክክር ጉባኤውን ዕለታዊ ሂደት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ከስምንቱም ቡድኖች የተውጣጡ የምክክር ሃሳቦች አደራጅ ተሳታፊዎች ሥራቸውን ሢሠሩ እንደቆዩ ተናግረዋል።
የስምንቱንም ቡድን አጀንዳ አደራጅቶ ማቅረብ ጥንቃቄ የሚፈልግ ሥራ እንደመኾኑ የተወሰነ ጊዜ ወስዷል ብለዋል። አደራጅ ቡድኑም ጠንክሮ በመሥራት በስምንቱ አጀንዳዎች ላይ አንድ ወጥ የኾነ ሰነድ አዘጋጅተዋል ነው ያሉት።
የተዘጋጀው ሰነድም ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ለስምንቱም ቡድን እየቀረበ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ይህም እያንዳንዱ ቡድን በሚቀርበው ሰነድ ላይ የመጨረሻ ግብዓቱን እና አስተያየቱን መስጠት እንዲችል የተዘጋጀ ሂደት መኾኑንም ገልጸዋል። አደራጅ ቡድኖቹ የተሰጠውን ግብዓት የመቀበል እና ምክረ ሀሳብ የመስጠት ሥራ እየሠሩ መኾናቸውን ነው የተናገሩት።
እነዚህ ከስምቱ ቡድን የተውጣጡት 120ዎቹ አደራጆች ማምሻቸውን በሰነዱ ላይ የመጨረሻዎቹን ግብዓቶች በማካተት የመጨረሻውን ሰነድ አዘጋጅተው እንደሚያቀርቡም አስታውቀዋል።
በዚህ መሠረት የተደራጀው የመጨረሻው ሰነድ ነገ ለ4 ሺህዎቹ ተሳታፊ እንደሚቀርብም አስታውቀዋል። ይህም ታላቅ ምዕራፍ ላይ መድረሳችንን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ኮሚሽነሯ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳንድ የተዛቡ መረጃዎችን በመስማት እንዳይወዛገብ አሳስበዋል። ይልቁንም ትክክለኛ ሚዲያዎችን እና የኮሚሽኑን መግለጫዎች በመስማት ትክክለኛ መረጃ እንዲይዝ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየሻደይ ባሕላዊ ጨዋታን የቱሪዝም ማዕከል ማድረግ ይገባል።