
የትምህርት ሚኒስቴር የ2019 ዓ.ም የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን በሚመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው እንደ ሀገር አዳሪ ትምህት ቤቶች ከአምስት ወደ ዘጠኝ ማደጋቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ሕይወት ተናግረዋል።
አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታው እንደገለጹት አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም ክልሎች ሥራ መጀመራቸውን ጠቅሰዋል። ሁሉም አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከ250 በላይ አዳዲስ ተማሪዎችን እንደሚያስተናግዱ ተናግረዋል። አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ጥራት ያላቸው ጠቀሜታ ትልቅ መኾኑን ገልጸዋል።
ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስተናግድ ዝግጁ መኾናቸው ተናግረዋል። የ9ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አማካይ ውጤት 85 በመቶ እና በላይ ያለው/ያላት እንዲኹም በእንግሊዝኛ እና በሒሳብ ትምህርቶች 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች መኾን ይገባቸዋል ብለዋል።
የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በሚሰጥባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ለመማር ፍላጎቱ ያላቸው እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎች በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ የሚችሉ መኾኑ ተገልጿል።
ዘጋቢ: ራሄል ደምሰው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
