ሻደይ – የክረምቱም የገበያውም ድምቀት

7
ሻደይ ከባሕላዊ የልጃገረዶች ጨዋታነት ባለፈ ትልቅ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ በዓልም ነው። በሰቆጣ ከተማ ማክሰኞ ገበያ ላይ ለሻደይ የሚዋቡበትን ጌጣጌጥ ሲገዙ ያገኘናቸው አቨገሸይ እና ጥሩነሽ ኪሮስ ሻደይ ሲመጣ ገበያው በባሕላዊ ጌጣጌጦች እና አልባሳት ይሞላል ብለዋል።
ለሻደይ የሚኾናቸውን ጌጣጌጦች በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዙ መኾኑንም አጫውተውናል።
የሻደይ ገበያ ለሻደይ ብቻ የሚያገለግሉ ጌጣጌጦችን፣ አልባሳትን እና ባሕላዊ እቃዎችን የሚያቀርቡበት መኾኑን ነጋዴ ጥላዬ ሳሞል ተናግረዋል።
ለሻደይ ገበያም ድሪ፣ ስንድድ፣ ላስቲክ ጫማ፣ ድኮት፣ ማርደ፣ ጥሩራ፣ መልጎም የመሣሠሉትን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረባቸውን ነው የገለጹልን።
ሻደይ የቀዘቀዘውን ገበያ የሚያነቃቃ፤ የክረምቱን ብርድ የሚያሞቅ ትልቅ አቅም ያለው በዓል መኾኑን የተናገሩት ደግሞ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ይርጋ ማርዬ ናቸው።
የሻደይን በዓልም ከንግድ እና ባዛር ጋር በማስተሳሰር ለማክበር መዘጋጀታቸውንም ኀላፊው ገልጸዋል። በቀጣይም ሻደይን ለዋግ ኽምራ ትልቅ የኢኮኖሚ ምንጭ ለማድረግ ከአጋር ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት መዘጋጀታቸውን አቶ ይርጋ ማርዬ ጠቅሰዋል።
የሻደይ ባሕላዊ ጨዋታ በዞን ደረጃ ሰቆጣ ከተማ ሊከበር በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ቀርተውታል።
በደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየመረጃ ቋት ለምን ይጠቅማል?
Next articleከቀጣናዊ ስጋቶች በላይ ከፍ ብሎ የተቀመጠው የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት