የመረጃ ቋት ለምን ይጠቅማል?

10
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመረጃ ቋት የተደራጁ መረጃዎች ደኅንነታቸው በተጠበቀ መንገድ በአንድ ቦታ ለማስቀመጥ፣ ለማሥተዳደር እና በቀላሉ ለመጠቀም የሚያስችል የዲጂታል መረጃ ቋት እንደኾነ ” IBM” የተባለው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መረጃ ያሳያል።
​ዋና ዋና የመረጃ ቋት ዓይነቶች
👉ተዛማጅ የመረጃ ቋት (Relational Database)፦ መረጃዎችን በሰንጠረዥ (በRows እና Columns) ያደራጃል። እንደ ፋይናንስ ነክ ሰነዶች እና ቁጥራዊ መረጃዎች ያሉ የተዋቀሩ መረጃዎችን ለመያዝ ተመራጭ ነው።
👉ተዛማጅ ያልኾነ የመረጃ ቋት ፦ እንደ ጽሑፍ፣ ድምጽ እና ቪዲዮ ያሉ ያልተዋቀሩ መረጃዎችን ለማደራጀት ያገለግላል።
👉ቬክተር የመረጃ ቋት፦ መረጃዎችን በዲጂታል ኮድ መልክ የሚያስቀምጥ ነው። በብዛት ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መተግበሪያዎች ጥቅም ላይ ይውላል።
✍️ለተቋማት የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው?
#የመረጃ ማረጋገጫ (Fact-Checking) ቡድኖች በርካታ መረጃዎችን ለማደራጀት ያግዛቸዋል።
#ማዕከላዊ አሥተዳደር፦ መረጃዎችን በአንድ ቦታ በመቆጣጠር በቀላሉ ማግኘት እና መጠቀም ያስችላል።
#ደኅንነት እና ትክክለኛነት፦ መረጃዎች እንዳይደለዙ፣ እንዳይቀየሩ ወይም ላልተፈቀደለት አካል እንዳይጋለጡ ይከላከላል።
#ለኤአይ (AI) እና ምርምር መሠረት መኾን፦ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ለምርምር ሥራዎች ጥራት ያለው መረጃ ያቀርባል።
#መረጃን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ዳታቤዝ ቀደም ሲል የተሠሩ ፍተሻዎችን፣ የተረጋገጡ ምስሎችን እና የታመኑ ምንጮችን በአንድ ቦታ አደራጅቶ በመያዝ አዲስ የሚመጡ አጠራጣሪ መረጃዎችን በፍጥነት ለማዛመድ እና ለማረጋገጥ ያገለግላል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article🕊️ ከአፈሙዝ ጩኸት ወደ አዕምሮ ከፍታ – የዕውነተኛ ጀግንነት ምልክት
Next articleሻደይ – የክረምቱም የገበያውም ድምቀት