የሻደይ በዓል በሰላም እንዲከበር የጸጥታ መዋቅሩ ዝግጅቱን አጠናቋል።

5
የሻደይ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲውል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ መኾኑን የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮማንደር አምበሉ ጥላሁን ሻደይ ለሴቶች እና ለወጣቶች የነጻነት ቀን መኾኑን ገልጸዋል።
በዓሉ ሃይማኖታዊ ይዘቱን እና ባሕላዊ ትውፊቱን ጠብቆ በሰላም ተከብሮ እንዲውል የፖሊስ መዋቅሩ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመኾን በጥምረት እየሠራ እንደኾነ ነው የገለጹት።
ሻደይ ሲከበር ፍቅርን፣ ሰላምን እና አንድነትን መሠረት ባደረገ መልኩ ሊኾን ይገባል ብለዋል።
ሕዝቡ በሀሰተኛ የማኅበራዊ ሚዲያ ወሬዎች ሳይደናገር በዓሉን በነጻነት ማክበር አለበት ነው ያሉት። የጸጥታ መዋቅሩም አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አንስተዋል።
የዋግ ኽምራ ሕዝብ ሰላም ወዳድ ነው ያሉት ኮማንደር አምበሉ ጥላሁን አሁንም ከጸጥታ መዋቅሩ ጎን እንዲኾን ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦ ሙላት ክንፉ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኾነው ተሾሙ።
Next articleበቱሪስት ከተማዋ ደባርቅ እየተከናወነ ያለው የልማት ሥራ ለንግድና ለቱሪዝም ዕድገት አዲስ ተስፋ ፈንጥቋል።