
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ አድርገው ሾመዋል።
በሌላ በኩል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኾነው ሲያገለግሉ የቆዩት ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኾነው መሾማቸው ታውቋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለሁለቱም ከፍተኛ መሪዎች የሥራ ዘመናቸው ስኬታማ እንዲኾን ተመኝቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
