‎”ለማን እንደምንታገል ሳናውቅ የምናደርገው ዓላማ የሌለው ትግል በመኾኑ ተጸጽተን መጥተናል” ወደ ሰላም የተመለሱ ታጣቂዎች

5


‎በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ ዙሪያ «ዓለምሳጋ» በተባለ ቦታ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 12 የታጣቂ ቡድን አባላት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ ኮር እጃቸውን ሰጥተዋል።

‎በሀገር መከላከያ ሠራዊት የቀጣናው ኮር አዛዥ ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ እንዳስታወቁት ታጣቂዎቹ የሰላምን መንገድ እንዲመርጡ የኮር፣ የአድማ መከላከል እና የሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች መሪዎች በቅንጅት ሠርተዋል።

‎ወደ ሰላም ከተመለሱት 12 አባላት መካከል ስምንቱ ከነሙሉ ትጥቃቸው መግባታቸውንም አረጋግጠዋል።

‎ወደ ሰላም ከተመለሱት አባላት መካከል የቡድኑ የብርጌድ አዛዥ ሰጥአረገው እሸቴ፣ የሻለቃ አዛዥ ስመኘው አረዓያ እና የሻምበል አዛዥ አንሙት ፀጋዬ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

‎ወደ ሰላም የተመለሱት ታጣቂዎች በበኩላቸው «ጫካ መግባት ትርጉም የሌለው፣ ለማን እንደምንታገል እና እንደምንሞት ሳናውቅ የምናደርገው ዓላማ የሌለው ትግል በመኾኑ ተጸጽተን መጥተናል» ብለዋል።

‎አክለውም የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ እና የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል። ዘገባው የምሥራቅ እዝ ነው

‎#አሚኮ #ሰላም #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

‎#ደብረ_ታቦር #መስከረም_06_2019_ዓ_ም

‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“የነገው ስኬት ዛሬ ይጀምራል” የ2019 በጀት ዓመት ትምህርት በዋግ ኽምራ