“የነገው ስኬት ዛሬ ይጀምራል” የ2019 በጀት ዓመት ትምህርት በዋግ ኽምራ

0

 

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች ከመስከረም 5/2019 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሂደቱ ተጀምሯል።

ተማሪ በረከት ሙሉጌታ እና ተማሪ ዳዊት ደሳለኝ በመድኃኔዓለም አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ4ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው። በትምህርታቸውም እርስ በእርስ ተፎካካሪ እንደኾኑ አጫውተውናል። በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርትም በጋራ ሲማሩ እንደነበረ ያስታወሱት ተማሪዎቹ ትምህርትን ከመስከረም እስከ ሰኔ ያለማቆራረጥ መማር ለውጤታማነት አንዱ መንገድ ነው ብለዋል።

ቀድመው ትምህርት ለጀመሩ ተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍትን ማከፋፈል መጀመራቸውን የተናገሩት ደግሞ የመድኃኔዓለም አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ኃይለሚካኤል ወንዳጥር ናቸው። ወላጆችም ልጆቻቸውን እንዲልኩ ጥሪ አቅርበዋል።

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሁሉም ወረዳዎች ትምህርት መጀመሩ ሕጻናት በየአካባቢያቸው ትምህርት እንዲያገኙ ዕድል መፍጠሩን የገለጹት ደግሞ የትምህርት መምሪያ ኀላፊው ሰይፈ ሞገስ ናቸው። እስካሁን ወደ ትምህርት ቤት ያልመጡ ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ማድረግ የወላጆች ሚና ጭምር መኾኑን ነው የተናገሩት። ተማሪዎችም የምዝገባ ጊዜው ሳይጠናቀቅ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

#አሚኮ #education #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ሰቆጣ #መስከረም_06_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleያለፉት ዓመታት የሰላም ጥረቶች አማራ ክልልን ከየት ወደ የት?
Next article‎”ለማን እንደምንታገል ሳናውቅ የምናደርገው ዓላማ የሌለው ትግል በመኾኑ ተጸጽተን መጥተናል” ወደ ሰላም የተመለሱ ታጣቂዎች