“የተከዜ ፖለቲካ” መጽሐፍ በስሜት ሳይኾን በስሌት የተጻፈ ብርቱ ሰነድ ነው።

18
የደራሲ ቹቹ አለባቸው (ዶ.ር) “የተከዜ ፖለቲካ” መጽሐፍ በደብረ ታቦር ከተማ ተመርቋል።
የደራሲ ቹቹ አለባቸው (ዶ.ር) “የተከዜ ፖለቲካ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ የዞን እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች እና የክብር እንግዶች በተገኙበት በደብረ ታቦር ከተማ ተመርቋል። በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን መጽሐፉ ታላቅ ሀገርን ከታሪካዊ አውድ ጋር በማቆራኘት ለንባብ መብቃቱ ለትውልድ ትልቅ ትርጉም ያለው መኾኑን ገልጸዋል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ መጽሐፉ በስሜት ሳይኾን በስሌት የተጻፈ እና የሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል በመዳሰስ ለሀገር ዕድገት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ብርቱ ሰነድ መኾኑን ጠቁመዋል።
አንባቢያን “የተከዜ ፖለቲካ” ከወንዝ ፍሰት ባለፈ ያለውን የጂኦፖለቲካ ይዘት በመረዳት ቀጣናውን ለማስተሳሰር ያላቸውን ድርሻ መገንዘብ እንዳለባቸው ተናግረዋል። ደራሲው ላበረከቱት አስተዋጽኦም አድናቆታቸውን ችረዋል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተሳተፉት እንግዶችም ተከዜ ለኢትዮጵያ እንደ “ሆርሙዝ” ቀጣና ወሳኝ ቀጣናዊ የፖለቲካ ይዘት ያለው ቦታ መኾኑን ገልጸዋል።
አካባቢው የወርቅ ምድር በመኾኑ እንዳሻቸው መጠቀም የሚናፍቁ ኀይሎች ከትናንት እስከ ዛሬ የሚፈልጉት እና የማያገኙት ታሪካዊ ቦታ መኾኑንም አንስተዋል።
ዘጋቢ፦ ተክለብርሃን ፈንታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየእንግጫ ነቀላ እና ከስይ አጨዳ ባሕላዊ እሴቶችን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተሠራ ነው።