🏫 📚ኢዜአ በባሕር ዳር ከተማ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መማሪያ ክፍሎች ግንባታ አስጀመረ።

8

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በ7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ወጭ ለሚያስገነባው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች በከተማው በምሥራቅ ግዮን አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ አስጀምሯል።

የኢዜአ ምክትል ሥራ አሥፈጻሚ ምንይችል ዓለማየሁ የሚዲያ ተቋሙ ማኅበረሰቡን የማስተማር እና መረጃ ተደራሽ የማድረግ ተልዕኮውን እየተወጣ መኾኑን ገልጸዋል።

በተለይም በመረጃ ማኅበረሰቡን ከማንቃት ባለፈ ተቋሙ በክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባራት እያከናወነ መኾኑን ነው የተናገሩት። ተቋሙ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን እየተወጣ መኾኑንም አመላክተዋል።

በባሕር ዳር ከተማም በ7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር አራት መማሪያ ክፍሎች ያሉት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
አንድ ብሎክ ለመገንባት የመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጣቸውንም ጠቁመዋል። ተቋሙ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን እየተወጣ መኾኑንም አመላክተዋል። ይህ ተግባር እስኪጠናቀቅ ድርስ ክትትል እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል።

ትውልድን የመገንባት ሥራ እየተሠራ ነው ያሉት ምክትል ሥራ አሥፈፃሚው ተግባሩ ዛሬ ትውልድ የሚታነጽበት ነገ ደግሞ ሀገር የሚገነባበት ነው ብለዋል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ በክረምት የበጎ ፈቃድ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልም የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ መቅረጽ ነው ብለዋል። የሚገነባው የመማሪያ ክፍልም ለታዳጊ ሕጻናት እና ለሀገር ተረካቢዎች መሠረት ለመጣል ያግዛል ነው ያሉት። ይህም በትምህርት ጥራት ላይ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው ብለዋል። ለተደረገው ተግባርም አመሥግነዋል።

የአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ወንድይራድ በቀለ እና የምሥራቅ ግዮን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርት አያል እምቢያለ በትምህርት ቤቱ በተለይም የቅድመ ሕጻናት የመማሪያ ክፍል እጥረት የነበረ መኾኑን አንስተዋል። ይህ የሚገነባ መማሪያ ክፍልም የነበረውን ችግር ሊፈታ የሚችል የመሠረተ ልማት ነው ብለዋል።

በዕለቱ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የተከናወነ ሲኾን ዓለም አቀፍ የወጣቶችን ቀን ምክንያት በማድረግም ከወጣቶች ጋር የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

#Ameco #ትምህርት #Ethiopia #ENA🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_09_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ:-ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበጋራ ቁርጠኝነት ትምህርት ቤቶችን መክፈት፣ መልሶ መገንባት እና ተስፋን መዝራት ያስፈልጋል።
Next articleወልቃይት ጠገዴ የኢትዮጵያ ሳንባ ናት ፤ ተከዜ ደግሞ የደኅንነት እና የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው!