
“5ኛው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ቻሌንጅ” መርሐግብር በኢንፎርሜሽን መረብ ደኀንነት አሥተዳደር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል።
የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሃሚድ የሳይበር ቴክኖሎጂ ዕድገት ለኢትዮጵያ የሳይበር ደኅንነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስኬት መሠረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል።
በዕውቀት፣ በሙያ እና በሥነ-ምግባር የበለጸገ ትውልድ ለሀገር ማፍራት የሰመር ካምፑ ዓላማ መኾኑን ዋና ዳይሬክተሯ ትዕግሥት ሃሚድ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የዲጂታል 2030 ስትራቴጂን ቀርጻ እየሠራች በመኾኑ የዛሬዎቹ ሠልጣኞች ለዚህ ስኬት የሚተጉ የቀጣዩ ትውልድ የዲጂታል ባለሙያዎች እንደኾኑም ጠቁመዋል።
የሀገሪቱ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት የሚረጋገጠው በዕውቀት የበለጸገ እና በቴክኖሎጂ የተራቀቀ ትውልድ በመፍጠር መኾኑንም ዋና ዳይሬክተሯ አስገንዝበዋል።
መርሐግብሩ ከቀደሙት ዓመታት በተለየ መልኩ በስድስት ዩኒቨርሲቲዎች መካሄዱም ተገልጿል።
በሥልጠናው ከ1ሺህ 200 በላይ ወጣቶች እየተሳተፉ መኾኑም ተመላክቷል።
በማስጀመሪያ መርሐግብሩ ወጣቶቹ በሥልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀት እና ክህሎት ለሀገር ጥቅም እንዲያውሉም ጥሪ ቀርቧል።
ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
