ግብርና ሚኒስቴር በ26 ሚሊዮን ብር ወጭ በመርዓዊ ከተማ የዘመናዊ ትምህርት ቤት ግንባታ ጀመረ።

4
የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ተገኝተው ዘመናዊ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታውን አስጀምረዋል።
ትምህርት ቤቱ ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ በጀት በግብርና ሚኒስቴር የሚገነባ መኾኑ ተገልጿል።
በተያዘው በጀት ዓመት በመርዓዊ እና አዴት ከተማ ሁለት የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡም ተነግሯል።
የሥራ ኀላፊዎቹ በመርዓዊ ከተማ የተገነባውን የኮሪደር ልማት በመመረቅ በመገንባት ላይ የሚገኙ የሕዝብ መሠብሠቢያ አዳራሽ እና ሌሎች የልማት ሥራዎችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በከተማዋ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርም አከናውነዋል።
በመርሐ ግብሩ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ እያሱ ኤልያስ (ፕ.ር)፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ኀላፊ መስፍን አበጀን (ዶ.ር) እና ሌሎችም የግብርና ሚኒስቴር፣ የክልል፣ የዞን እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
✍️ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ተስፋ ሰጭ እርምጃዎች