ዜናአማራየእለቱ አበይት ዜና ዋና ዋና ነጥቦች፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ቆይታ August 9, 2026 44 ያልተቀደሰ ጥምረት፦ በኦሮሚያ፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲረዱ ያልተቀደሰ ጋብቻ/ጥምረት ፈጥረዋል። አሮጌ የፖለቲካ አስተሳሰብ፦ የሕወሓት ቡድን ዛሬ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሊሰካ በማይችል፣ በአሮጌ የፖለቲካ ሀሳብ እና አመራር ውስጥ ተቀርቅሮ ይገኛል። ታጣቂዎችን መሣሪያ ማድረግ፦ ቡድኑ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ ታጣቂዎችን እንደ እኩል አጋር ሳይሆን ሀገርን ለማፍረስ እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ እያደረጋቸው ነው። የውጭ ጠላቶች ፍላጎት ማገልገል፦ ኢትዮጵያን የማዳከም እና የመበተን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ፍላጎት ላላቸው ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች መሣሪያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ወደ ሕግ የበላይነት መሸጋገር፦ እውነተኛ ዲሞክራሲ ከፖለቲካ ነፃነት ወደ ምክክር፣ ምክክር ደግሞ በጋራ ስምምነት ወደሚቀረጽ የሕግ የበላይነት ማደግ አለበት። #PMOEthiopia ተዛማች ዜናዎች:ሃብት ትርጉም የሚኖረው ለተቸገሩ ወገኖች ሲተርፍ ነው።