ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/12/18 ዓ.ም (አሚኮ) ሜታ ማኅበራዊ ሚዲያው በልጆች ላይ የደቀነውን አደጋ በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ባለመስጠቱ ተደጋጋሚ ክስ ቀርቦበታል።
ከሰሞኑም በአሜሪካ ኒው ሜክሲኮ ፍርድ ቤት በተላለፈበት ውሳኔ የልጆችን ደኅንነት ከመጠበቅ ጋር በተያያዘ 567 ሚሊዮን ዶላር እንዲቀጣ ተወስኖበታል።
ማኅበራዊ ሚዲያው በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው ጫና ከየአየር ብክለት ጋር የሚመጣጠን ተብሎም ቀርቧል።
ሜታ በቀረበበት ተመሳሳይ ክስ ከዚህ በፊት 373 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተወስኖበት ነበር። የአኹኑ ሲደመርም አጠቃላይ ቅጣቱ 942 ሚሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ቢቢሲ አስነብቧል።
ሜታ ላይ የቀረበው ዋና ክስ ይዘቶቹ “የሥነ ልቦና ጫና የሚያሳድሩ እና ልጆችን ለወሲብ ብዝበዛ የሚያጋልጡ ናቸው የሚል ነው።
ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ዋትስአፕ እና ትሬድስን የሚያስተዳድረው ሜታ ውሳኔውን እንደማይቀበል አስታውቋል።
“በመተግበሪያዎች ሰዎች ደኅንነታቸው እንዲጠብቁ ብዙ ተሠርቷል፤ መጥፎ ድርጊት የሚፈጽሙን እና ጎጂ ይዘትን በመለየት ረገድ ያለውን ፈተና በግልጽ አሳውቋል የሚል መከራከሪያም አንስቷል።
ሜታ ልጆችን ለአደጋ በመዳረጉ፣ ለልቅ ወሲባዊ ይዘት በማጋለጡ እና ወሲባዊ ጥቃት አድራሾች ባሉት መድረክ ከለላ ባለመስጠቱ በኒው ሜክሲኮ እንዲከሰስ የተወሰነው በ2023 ነበር።
አኹን ላይ በአሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ተመሳሳይ ክሶች ቀርበውበታል።
“ልጆች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ቤተሰቦቻቸው፣ ትምህርት ቤታቸው፣ ሆስፒታሎች እና የሕግ አስከባሪዎች ድረስ የሚዘልቅ ነው” ተብሏል።
ሜታ የሚቀጣው ገንዘብ ካደረሳቸው ጉዳቶች ለማገገም እንደሚውል በፍርድ ሂደቱ ተጠቅሷል።
በዚህ መሠረት 420 ሚሊዮን ዶላር ቅጣቱ ሜታ ካሳደረው “የጤና እና የሥነ ልቦና ቀውስ ለማገገም የሚሠሩ ባለሙያዎች እና መርሐ ግብሮች ላይ” የሚውል ይኾናል።
ቀሪው ገንዘብ ግንዛቤ ለመፍጠር እና መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ልጆችን ከማኅበራዊ ሚዲያ ጉዳት የሚጠብቁበት መንገድ ለመዘርጋት ይውላል።
#የሜታ መተግበሪያ ዕድሜያቸው ከ18 በታች የኾኑ ተጠቃሚዎችን ለአዋቂዎች ጥቆማ መስጠት እንዳይችሉ
#አዋቂዎች ለታዳጊዎች መልዕክት መላክም እንዳይችሉ
#ከ18 ዓመት በታች ለኾኑ ተጠቃሚዎች ‘ላይክ’ መቁጠር እንዳይቻል
#የድረ ገጹ ጥቆማ ከምሽት እስከ ንጋት ለታዳጊዎች እንዳይላክ እና ከቅዳሜ እና እሑድ ውጭ በትምህርት ሰዓት ጥቆማ እንዳይላክ
#ተጠቃሚዎች በወር ውስጥ ኢንስታግራም እና ፌስቡክ የሚጠቀሙበት ሰዓት ከ90 ተከታታይ ሰዓት እንዳያልፍ ወሳኔ ተላልፎበታል።
በቀጣይ ሜታ ከልጆች ደኅንነት ጥበቃ ጋር በተያያዘ ሌላ ትልቅ ክስ በካሊፎርንያ ይጠብቀዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
