
ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/12/18 ዓ.ም (አሚኮ) የበይነ መረብ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሕፃናት እና ታዳጊዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እየበዙ ነው።
በኢትዮጵያ ከ3መቶ ሺ በላይ የሚጠጉ ታዳጊዎች የመስመር ላይ ብዝበዛ እና ጥቃቶች ሰለባ መኾናቸውን ኢንሳ ከወራት በፊት ባወጣው መረጃ ጠቁሟል።
#በኢንተርኔት አማካኝነት የሚፈጸም የሕፃናት ማታለል (Cyber Grooming)፦
የሳይበር አዳኞች የሕፃናትን አቻ ዕድሜ በመምሰል፣ የሐሰት ወዳጅነት በመመሥረት እና እንዲታመኑ በማድረግ ሚስጥራቸውን ተቀብለው ለወሲባዊ ብዝበዛ የሚያዘጋጁበት አደገኛ ስልት።
#ሴክስቶርሽን (Sextortion)፡ አጥቂዎች ከልጆች ያገኙትን የራቁት ወይም ወጣ ያሉ ምስሎችን ተጠቅመው “የፈለግኩትን ካላደረጋችሁ ምስሉን እበትነዋለሁ” በማለት ታዳጊዎችን ለከፋ ሥነ-ልቦናዊ ጫና የሚዳርጉበት የጥቃት አይነት ነው።
#የማኅበራዊ ሚዲያ ትንኮሳ ወይም ጉልበተኝነት (Cyber Bullying)፡-
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ታዳጊዎችን ስም ማጥፋት፣ ማሸማቀቅ እና የሚያንቋሽሹ መልዕክቶችን በመላክ ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ቀውስ የሚፈጥር ነው።
#በኢንተርኔት አማካኝነት ሰዎችን መከታተል ወይም ማስፈራራት (Cyber Stalking)፦
አጥፊዎች የሕፃናትን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እና የሚሄዱባቸውን ቦታዎች (Location) በድብቅ እየተከታተሉ የሚያደርሱት የትንኮሳ አይነት ነው።
ልጆች ከእነዚህ አደጋዎች እንዲጠበቁ በንቃት መከታተል አስፈላጊ ነው።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
