የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት፦

6
የአቪዬሽን መሠረተ ልማት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ምሰሶ ነው።
ዛሬ መርቀን አገልግሎት ያስጀመርነው የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል የአየር መንገዳችን ደማቅ የስኬት ጉዞ ማሳያ ነው።
ይህ ዘመናዊ ተርሚናል ለባሕር ዳርና ለአካባቢው ፈርጀ ብዙ ኢኮኖሚያው ፋይዳ ያለው ከመሆኑም በላይ፣ ከተማዋን ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቀጥሎ የሁለተኛው ትልቅ የዓለም አቀፍ አቪዬሽን ማዕከልነት ሚና እንዲኖራት የሚያስችል ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ የላቀ ጥራትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።
ከፍተኛ የማስተናገድ አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባው ይህ ደረጃውን የጠበቀ ተርሚናል፣ ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብቶችን ለመጎብኘት የሚመጡ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን በቀጥታና በምቾት ለማስተናገድ በዕጅጉ ይረዳል።
በተጨማሪም የንግድና የኢንቨስትመንት ፍሰቱን በመጨመር ምርቶችን በፍጥነት ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ፣ በአቪዬሽን፣ በሆቴልና በትራንስፖርት ዘርፎች ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር እንዲሁም ባሕር ዳርን የዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ሁነቶች ማዕከል ለማድረግ ከፍተኛ አቅምን ይፈጥራል።
ፕሮጀክቶችን አቅዶ መጀመር፣ በጥራት ፈጽሞ ለህዝብ አገልግሎት ማብቃት የመደመር መንግሥት ባህልና መገለጫ ነው፤ ይህ የትጋትና የመፈጸም ጉዟችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!
የውበት፣ የልምላሜና የፀዳል ተምሳሌት የሆነሽው ውቧ ባሕር ዳርና የአካባቢው ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ!
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በባሕር ዳር ከተማ ልማቶችን ጎበኙ።
Next article“ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ በርካታ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ