
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ከተማዋ ያላትን እምቅ አቅምና ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴዎች በግልጽ የታየ ሲሆን፤ እነዚህ ስትራቴጂካዊ የልማት ስራዎች የነዋሪዎቿን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ፣ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ መነቃቃትን የሚፈጥሩ እንዲሁም ከተማዋ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያላትን የንግድና የኢንቨስትመንት ማዕከልነት ሚና ይበልጥ የሚያጠናክሩ ናቸው።
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ ድጋፍ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርምም ለማየት ችለዋል።
