ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ታሪካዊ ግንኙነታቸውን እና ቀጣናዊ ስትራቴጂክ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።

1

 

የመከላከያ ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ከውጭ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር የሚያደርጉትን ተከታታይ

የወታደራዊ ዲፕሎማሲ ውይይት በመቀጠል፣ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጃሲንቶ ማሲንጋን በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራና በውጤት የታጀበ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባሕር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ መሆኗንም ገልጸዋል። ሁለቱ ሀገራት በቀጣናው መረጋጋት ላይ በቅርበት መሥራታቸው ዘርፈ ብዙ ውጤት ያለው መሆኑን አመላክተዋል።

በቅርብ ጊዜያት የሁለቱ ሀገራትን ስትራቴጂካዊ ወታደራዊ የስምምነት ማዕቀፍ መፈረም የአሜሪካ አምባሳደር እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ለተጫወቱት የጎላ ሚና ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ የሕዝቦቿን አሁናዊና ቀጣይ ፍላጎት ለመመለስ እና ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማስከበር

የምትጥር ሀገር መሆኗን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፤ አሜሪካም በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረተውን የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂክ አጋርነት መሰረት እያደረገች ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፏን አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል።

የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጃሲንቶ ማሲንጋ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከጊዜና ከሁኔታዎች የተሻገረ መሆኑን

ገልጸዋል። አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ቅድሚያ ሰጥታ እንደምትሠራም አረጋግጠዋል።

በቀጣናው ሽብርተኝነትን ለመከላከልና በወታደራዊ ዘርፍ የተጀመሩ ስትራቴጂካዊ ትብብሮችን አሜሪካ

አጠናክራ የምትቀጥል መኾኑን አምባሳደር ኤርቪን ገልጸዋል። መረጃው የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ነው።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_27_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

‎

Previous articleበሳምንት 230 ሺህ ጫጩት በማስፈልፈል ለገበያ ለማቅረብ የተዘጋጀው የኮምቦልቻ ዶሮ ሃብት ልማት ኢንተርፕራይዝ