የውበት ልኳ ባሕር ዳር

16
🌴
ባሕር ዳር ከተማ ውበቷን ይበልጥ እየገለጡ በሚገኙ ስኬታማ ልማቶች እየደመቀች የምትገኝ ከተማ ናት።
የኮሪደር ልማቶች፣ የዘመናዊ መሰረተ ልማት ግንባታዎች እና የጽዳትና አረንጓዴ ልማት ሥራዎች ከተማዋን በየዕለቱ የበለጠ እያደመቋት ይገኛሉ።
ይህ የሁሉም የወል ስኬት፣ የነገዋን ባሕር ዳር በጠንካራ መሰረት ላይ የመገንባት ጥረት ማሳያ መሆኑን የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጉሹ እንዳላማው አረጋግጠዋል።
​ከተማዋን በሁሉም መስክ ስማርት የማድረግ ጉዞ ተጠናክሮ የሚቀጥል ተግባር ነው። ባሕር ዳርን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ፣ ለጎብኚዎች ደግሞ የማይረሳ ትዝታ የምታሳድር ውብ መዳረሻ የማድረጉ ጉዞ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአሚኮ ጋር ባደረጉት ቆይታ የባሕር ዳርን ለውጥ አንስተዋል። ባሕር ዳር ለውጡን ተከትሎ በተሠሩላት ዘርፈ ብዙ ልማቶች በብዙ መልኩ መለወጧን አብራርተዋል። በልዩ ትኩረት የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶች ባሕር ዳርን እጅግ የተዋበች ከተማ አድርገዋታል ነው ያሉት።
ከለውጡ ማግስት በተለይም አዲሱ የዓባይ ድልድይ፣ የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አዲሱ ተርሚናል፣ ፈለገ ግዮን ሪዞርት እና ዘመናዊ የመንገድ መሰረተ ልማቶቿ ባሕር ዳርን እንድትዋብና ተመራጭ ከተማ እንድትሆን የተከናወኑ ስኬታማ ተግባሮች ናቸው ብለዋል።
ባሕር ዳር ዛሬም በማያቋርጥ ልማት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። ከተማዋ የሚሠሩ እጆችን የምታስመሠግን በየቀኑ የምትፈካ የውበት ልክ ብትባል አይበዛባትም። እናንተስ ባሕር ዳር በዚህ ወቅት ስለምትገኝበት ውብ ገጽታ ምን ይሰማቹሀል? በአስተያየት መስጫው ሀሳብዎን ያካፍሉን።
በሀብተጊዮርጊስ አበይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleሰላም ለሁሉም ናት፤ ስለሰላም ሁሉም ያገባዋል !
Next articleየዘመናት ቋጠሮዎችን በመፍታት አዲስ የፖለቲካ ባሕል የመገንባት ታሪካዊ ምዕራፍ።