
በአማራ ክልል ከ2015 ዓ.ም መገባደጃ ጀምሮ የተከሰተው የሰላም እጦት ጥሎት ያለፈው ጉዳት ጥልቅ እና ሁለንተናዊ ነው። ክልሉ የሀገሪቱ የግብርና ምርት የጀርባ አጥንት በመኾኑ ግጭቱ የንግድ መስመሮችን ዘግቶ፣ የግብዓት ሥርጭትን አጓድሎ እና የኢንቨስትመንት ፍሰቱን አቀጭጮ የኑሮ ውድነቱን ለሸማቹ ፈተና እንዲኾን አድርጎት ቆይቷል።
በትምህርት እና በጤና ተቋማት መዘጋት፤ በዜጎች መፈናቀል፣ በትውልዱ ላይ በሰፈነው ስጋት እና ጭንቀት ሳቢያ ማኅበራዊ እና ሥነ-ልቦናዊ መስተጋብሩ ክፉኛ ተጎድቷል። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ስጋት ውስጥም ቢኾን የሕዝቡ የሥራ ወኔ እና የማይበገር ተስፋ አልተሰበረም። አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች ላባቸውን እያፈሰሱ ያስመዘገቧቸው የልማት ውጤቶች ለነገው ብሩህ ቀን ያለውን ጽናት የሚያሳዩ ህያው ምስክሮች በመኾን ይነሳሉ።
ችግሩ ጊዜ ሳይወስድ በዘላቂነት መፈታት እንዳለበት የሁሉም ፍላጎት ነው። ችግሮች በጠመንጃ አፈሙዝ ሳይኾን በጠረጴዛ እንዲፈቱ ቅድሚያ ለዚህ አካሄድ እንዲሰጥ የሰላም ፈላጊው ሕዝብ ጽኑ ፍላጎት ነው።
በሰላም ወጥቶ መግባት የማያሰጋበት ክልል እንዲኾን፤ ልጆቻችን እንዲማሩ፤ የነገ ተስፋችን እንዳይጨልም፤ ያለምንም ስጋት ወደ ልማት ገብተን ያመረትነውን በነጻነት ለገበያ እንድናቀርብ፤ መገዳደል ይብቃን፤ የሰላም አጋዥ ኾነን ሰላማችንን ማረጋገጥ ዋናው ፍላጎታችን የሚሉ ድምጾች በየመድረኩ ተሰምተዋል።
ይህ እውነተኛ እና መሪር ሕዝባዊ ጩኸት አሁን ላይ ፍሬ ማፍራት ጀምሯል፤ በክልሉ ውስጥ የሚነፍሰው የሰላም አየር መሻሻሎችን እያሳየ፤ የጠመንጃ ድምፅ እየቀነሰ የትጥቅ ትግል በቃኝ የሚሉ ድምጾች ጎልተው መሰማት ጀምረዋል።
መንግሥት ይህን አስከፊ ቀውስ ለመቀልበስ:-
የክልሉ ሰላም በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲቆም እና ዘላቂ እንዲኾን ግን አሁንም በቅንጅት መሥራት ይገባል ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በቅርቡ በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ግጭት እና ጦርነት ወደ ድል
ስለማይወስድ የመንግሥት ፍላጎት የታጠቁ ወገኖች በድርድር እንዲመለሱ ማድረግ ነው ብለዋል። በአማራ እና በኦሮሚያ ክክሎች ታጥቀው
የሚንቀሳቀሱ በርካታ ወገኖች የሰላምን አማራጭ መቀበላቸውን ገልጸዋል። ሌሎችም ሰላማዊ የትግል አማራጭን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
