በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ። 🇪🇹

8

 

🇪🇹በኢትዮጵያ ባለፋት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የላቀ ውጤት መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በሰጡት ማብራሪያ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተውም :-

📌 ባለፉት አምሥት ዓመታት አጠቃላይ የግብርና ምርት ከ44 ሚሊዮን ቶን ወደ 150 ሚሊዮን ቶን አድጓል። በዚህም ከ3 እጥፍ በላይ የምርት ዕድገት አምጥቷል።

📌 የደን ሽፋን ከ17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ አድጓል። ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግምም ተደርጓል።

📌 በ2018 በጀት ዓመት 29 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ምርትም ተሠብሥቧል።

👉 ቡናን ለውጭ ገበያ በማቅረብ በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል። ይህም የ17 ዓመታት የቡና ምርት ገቢን በአንድ ዓመት ማሳካት የተቻለበት ታሪካዊ ስኬት ኾኗል።

👉 ቀደም ሲል ስንዴን ከውጭ በማስገባት በርካታ ዶላር ታወጣ የነበረውን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ወደ ውጭ እየላከች የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ጀምራለች።🌾

📌 በድርቅ የሚታወቁት አካባቢዎች ምርታማ እየኾኑ ነው። ታርሰው የማያውቁ ሥፍራዎች በግብርና ልማት ተሸንፈዋል። ታይቶ የማይታወቅ ምርትም እየሰጡ ነው።

📌 የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረው የሌማት ቱርፋት መርሐ ግብር አስገራሚ ውጤት ተገኝቶበታል።

👉 የዶሮ ስጋ ምርት ከ8 ሺህ ቶን ወደ 190 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። ይህም የ296 በመቶ ጭማሪ እንዳለ ያሳያል።

👉 የአቮካዶ፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ሌሎችንም የፍራፍሬ አይነቶች በስፋት በማምረት ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ኾኗል። ለአብነትም በአቮካዶ ምርት በአፍሪካ ሁለተኛዋ ለውጭ ገበያ የምታቀርብ ሀገር መኾን ችላለች።

📊 ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ያለው ተጨባጭ ለውጥ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ግስጋሴዋን እንድታስቀጥል የሚያስችላት ስለመኾኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸው አይዘነጋም።

#አሚኮ #አማራክልል #Agriculture #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጳጉሜን_01_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበደቡብ ጎንደር ዞን ያለውን ሰፊ የብረት ማዕድን እና የድንጋይ ከሰል ሃብት ለማውጣት ጥረት እየተደረገ ነው።