
የዞብል ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ጀማል አማን በመርሀ ግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት “ሰላምን ማስጠበቅ የሁሉም ኅላፊነት ነው፤ የዛሬ ተመራቂዎችም ሰላምን ለማጽናት እና የሕዝባችሁን ደህንነት ለመጠበቅ በግንባር ቀደምትነት በመሰለፋችሁ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል” ብለዋል።
የሰከላ ወረዳ አሥተዳዳሪ አለማየሁ አዳነ ሰላም አስከባሪ መኾን ዩኒፎርም መልበስ ወይም መሳሪያ መያዝ ብቻ ሳይኾን፣ ፍትሕን መጠበቅ፣ የሰውን ማክበር፣ ሕግን ማስከበር እና ማኅበረሰብን በታማኝነት ማገልገል የሚጠይቅ ክቡር ኀላፊነት ነው ብለዋል። የዛሬ ተመራቂዎችም ይህንን በውል በመረዳት ወደተግባር መተርጎም እና ሕዝብን ማገልገል እንዳለባቸውም አሥተዳዳሪው ተናግረዋል። ከሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ሥልጠና ያገኙት ዕውቀት እና ክህሎት የሕዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ፣ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና የሕግ የበላይነትን ለማጠናከር መሠረት የሚኾን ነውም ብለዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡ ተመራቂዎችም የማኅበረሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ በቁርጠኝነት፣ በታማኝነት እና በቅንነት እንደሚሩ አስታውቀው በሥልጠናው የተሻለ አቅም እንደፈጠሩ ተናግረዋል።
በዕለቱ ለሥልጠናው መሳካት ጉልህ አበርክቶ ለነበራቸውና በሥልጠናው የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ አካላት እውቅና እና ምስጋና ተሰጥቷቸዋል።
ዘገባው የምሥራቅ ዕዝ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ!
