በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር የተመረቁ የጸጥታ ኀይሎች ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ተዘጋጅተዋል።

23
በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ለሀገዊ ተልዕኮ ዝግጁ ለመሆን ሲሠለጥኑ የቆዩ የደጀን ኀይል የፀጥታ አባላት ተመርቀዋል።
​ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ለተከታታይ ቀናት ሲሠለጥኑ የቆዩ ጥምር የፀጥታ ኃይሎች ሥልጠናቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል።
ተመራቂዎች ​የሀገርን ነፃነትና ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ታሪካዊ አደራን የመጠበቅ ኀላፊነት እንዳለባቸው ተመላክቷል።
የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር አብራራው አበጀ እና የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ መምሪያ ኀላፊ ብሩክ አለምነው በምረቃ ፕሮግራሙ ተመራቂዎችን አበረታተዋል። መረጃው የ​ደብረ ታቦር ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ800 ሚሊዮን ብር የቆዳ እና የጫማ ኢንዱስትሪ ለማቋቋም ስምምነት ተፈራረመ።
Next articleሕዝብ ያመነው ኃይል መቼም ቢሆን ድል ያደርጋል!