
በዳንግላ ከተማ በዘንድሮዉ ዓመት የተገነቡ መሰረተ ልማቶች የተመረቁ ሲሆን በዕለቱ የክብር እንግዳ ሆነዉ ሪቫን የቆረጡት የምስራቅ ዕዝ ኮር አዛዥ ብርጋዴል ጀኔራል አዲሱ ማህመድ እንደተናገሩት ፦ የአማራን ሕዝብ ስም እየሸጡ ለአማራ ታገልን እያሉ ሕዝብን የሚዘርፉ፣ የሚያግቱ እና አማራ እንዳይለማና እንዳያድግ እንቅፋት የሆኑ የነዘመነ ካሴ ጭፍሮችና ግብረ አበሮቻቸው ሕዝባችን ለርሀብና ለስደት ለመዳረግ ሴራ ጠንስሰዉ ቢሠሩም ሠራዊቱ በፅናትና መስዋዕትነት ከኅብረተሰቡና ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአካባቢዉ ሰላም እንዲረጋገጥና መሠረተ ልማቶች እንዲገነቡ እና እንዲመረቁ አስተዋፅኦዉ ከፍተኛ ነዉ ብለዋል ።
የዳንግላ ወረዳ አስተዳዳሪ ዋህቤ ፀጋ እንደገለፁት፡ ደኅንነትና ልማት ዋጋ ለሚከፍለው ጀግናው ሠራዊት ከፍተኛ አድናቆታቸውን አቅርበዋል።
ሠራዊቱ ከሰላም ማስከበር ሥራው ጎን ለጎን ለልማት ያበረከተው አስተዋጽኦ ታሪካዊ ነው። ከሠራዊቱና ከክልላችን ጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የተከናወኑት የገጠር መንገድ ፣ ከተማ ኮሪደር ፣ ጤና ተቋማት ፣ ግብርና የትምርት ተቋማት ሥራዎች የሕዝባችንን ኑሮ ከመለወጥ ባለፈ ለቀጣይ የልማት ምዕራፎች ትልቅ መሠረት የጣሉ መሆናቸዉን አብራርተዋል ።
በዕለቱ የኮሩ ወታደራዊ አመራሮችና የወረዳዉ አመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በዕለቱም የተዘጋጀዉን የፎቶ ኤግዚቢሽን ተመልክተዋል ። መረጃው የምስራቅ ዕዝ ነዉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
