የአማራ ክልል ፕላን ኢንስቲትዩት ከ130 በላይ ፕላኖችን አዘጋጅቶ ለከተሞች ማስረከብ ችሏል።

13
የአማራ ክልል ፕላን ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ.ም የነበረውን የተቋም አፈጻጸም አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ምትኩ ዓለማየሁ (ዶ.ር) በሰጡት መግለጫ በበጀት ዓመቱ የፕላን ለውጦች ሲኖሩ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ መመሪያዎችን ማዘጋጀት መቻሉን ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ በክልሉ በአጠቃላይ 137 ፕላኖችን አዘጋጅቶ ለከተሞች ማስረከቡን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ ከተዘጋጁት መካከል ሦሥት መዋቅራዊ፣ ሰባት የስትራቴጂክ፣ 44 መሠረታዊ፣ 39 የገጠር ቀበሌ ማዕከላት፣ 41 የሰፈር ልማት ፕላኖች እና ሦሥት የከተማ ዲዛይኖች እንደሚገኙበት ገልጸዋል።
በፕላን ዝግጅት እና ዳታ ሥብሠባ ሂደት ከ14 ሺህ 900 በላይ የማኅበረሰብ አባላትን ማሳተፍ የተቻለ ሲሆኾን ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የመሬት ላይ መቆጣጠሪያ ነጥቦችም ተሠርተዋል ነው ያሉት።
እስካሁንም 69 ከተሞች ፕላኑን በምክር ቤት አጽድቀው ወደ ሥራ የገቡ ሲኾን 131 ሺህ 697 የፕላን ስምምነቶች ተደርገዋልም ነው ያሉት።
በተጨማሪም የፕላን አተገባበርን ለመከታተል በ11 ከተሞች የኦዲት ክንውን የተካሄደ ሲኾን ፕላኑ በአግባቡ እንዲተገበር ለ50 ከተሞች የቁጥጥር እና የልምድ ድጋፍ ስለመደረጉም አስገንዝበዋል።
ተቋሙ በቀጣይ 130 የገጠር ቀበሌ ማዕከላት ስኬች ፕላንን ጨምሮ በአጠቃላይ 187 ፕላኖችን ለመሥራት ማቀዱን ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
ዘጋቢ: ኪሩቤል ተሾመ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleለስልታዊ ቡድኖች የሚቀርቡ አጀንዳዎች እየተጠናቀቁ ነው፡፡
Next articleበዳንግላ ወረዳ ለተገነቡ መሠረተ ልማቶች የመከላከያ ሠራዊትና የክልሉ የጸጥታ ኀይል ሚና ከፍተኛ ነው።