ለስልታዊ ቡድኖች የሚቀርቡ አጀንዳዎች እየተጠናቀቁ ነው፡፡

10
10 አባላት ባሏቸው 400 ጥቃቅን ቡድኖች እንዲሁም 50 አባላት ባሏቸው 80 ቡድኖች የተነሱ የአጀንዳ ሃሳቦች 25 አባላት ባሏቸው 16 የቃለ ጉባኤ አጠናቃሪ ቡድኖች ተጠናቅረው 250 አባላት ላሏቸው 16 ስልታዊ ቡድኖች መቅረባቸው ይታወሳል፡፡
የተጠናቀረውን ቃለጉባኤ ያዳመጡ ባለ 250 አባላት ስልታዊ ቡድኖች አልተካተቱም፣ በተነሳው ልክ አልተብራሩም ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተው ቃለ ጉባኤው እንዲሻሻል አድርገዋል፡፡
በትላንትናው የሀገራዊ ምክክር ገባኤ ውሎ ደግሞ የባለሙያዎች ስብስብ (Panel of experts) በ500 አባላት ለተደራጁ 8 የአጀንዳ ቡድኖች ባለፉት ቀናት በተደረጉት የምክክር ሂደቶች በተነሱ ፅንሰ ሃሳቦች፣ ግልፅ ባልሆኑ ጉዳዮች እንዲሁም በተለያየ ረገድ ፅንፍ በያዙ አስተሳሰቦች ዙሪያ ገለፃ በማድረግ ለቃለ ጉባኤዎቹ መዳበር የሚያግዙ ሀሳቦችን አቅርበዋል፡፡
የስልታዊ ቡድን የአጀንዳ ሃሳቦችን በቃለ ጉባኤ የሚያጠናቅሩ የባለ 25 አባላት አጠናቃሪ ቡድኖችም ከትላንት ከሰዓት እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ የቀረቡ ሳይንሳዊ ማብራሪያዎችን እና ገለፃዎችን ተከትሎ ያጠናከሩትን ሃሳብ እንደገና ሲያዳብሩ ውለዋል፡፡
ይህ የዳበረ ቃለ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በሚኖረው የምክክር ውሎ 250 አባላት ላሏቸው 16 ስልታዊ ቡድኖች የሚቀርብ ይሆናል፡፡ መረጃው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleትውልድ የሚያሻግር የጸጥታ መዋቅር መገንባት ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ነው።
Next articleየአማራ ክልል ፕላን ኢንስቲትዩት ከ130 በላይ ፕላኖችን አዘጋጅቶ ለከተሞች ማስረከብ ችሏል።